ዘኁልቁ
25 እስራኤላውያን በሺቲም+ ይኖሩ በነበረበት ጊዜ ሕዝቡ ከሞዓብ ሴቶች ጋር የፆታ ብልግና መፈጸም ጀመረ።+ 2 ሴቶቹም ለአማልክታቸው ወደተሠዉት መሥዋዕቶች ሕዝቡን ጠሩ፤+ ሕዝቡም ከመሥዋዕቱ መብላት እንዲሁም ለእነሱ አማልክት መስገድ ጀመረ።+ 3 ስለዚህ እስራኤል የፌጎርን ባአል በማምለክ ተባበረ፤*+ ይሖዋም በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ። 4 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እየነደደ ያለው የይሖዋ ቁጣ ከእስራኤል ላይ እንዲመለስ የዚህን ሕዝብ መሪዎች* ሁሉ ወስደህ በጠራራ ፀሐይ* በይሖዋ ፊት ስቀላቸው።” 5 ከዚያም ሙሴ የእስራኤልን ዳኞች+ “እያንዳንዳችሁ በፌጎር ባአል አምልኮ የተባበረውን* የየራሳችሁን ሰው ግደሉ” አላቸው።+
6 ሆኖም ልክ በዚህ ጊዜ አንድ እስራኤላዊ፣ ሙሴና በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ እያለቀሰ ያለው የእስራኤል ማኅበረሰብ በሙሉ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት+ ይዞ ወደ ወንድሞቹ መጣ። 7 የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ+ ይህን ሲመለከት ከማኅበረሰቡ መሃል ወዲያው ብድግ ብሎ ጦር አነሳ። 8 ከዚያም እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ በመግባት ሁለቱንም ወጋቸው፤ እስራኤላዊውን ወጋው፤ እሷንም ሆዷ* ላይ ወጋት። በዚህ ጊዜ መቅሰፍቱ ከእስራኤል ልጆች ላይ ተወገደ።+ 9 በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች 24,000 ነበሩ።+
10 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 11 “የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ+ በመካከላቸው እኔን የሚቀናቀነኝን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ ቁጣዬ ከእስራኤል ሕዝብ ላይ እንዲመለስ አድርጓል።+ ስለዚህ እስራኤላውያንን እኔን ብቻ ለምን አላመለካችሁም ብዬ ጠራርጌ አላጠፋኋቸውም።+ 12 በዚህም የተነሳ ከእሱ ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እንደምገባ ንገረው። 13 ይህም አምላኩን የሚቀናቀነውን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ+ እንዲሁም ለእስራኤል ሕዝብ በማስተሰረዩ ለእሱና ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ+ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ሆኖ ያገለግላል።”
14 ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው ሟቹ እስራኤላዊ የስምዖናውያን አባቶች ቤት አለቃ የሆነው የሳሉ ልጅ ዚምሪ ነበር። 15 የተገደለችውም ምድያማዊት ሴት የጹር+ ልጅ ኮዝቢ ነበረች፤ ጹር በምድያም ካሉት የአባቶች ቤት ጎሳዎች የአንዱ መሪ ነበር።+
16 በኋላም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 17 “ምድያማውያንን አንገላቷቸው፤ እንዲሁም ፍጇቸው፤+ 18 ምክንያቱም እነሱ ከፌጎርና+ ከእህታቸው ከኮዝቢ ጋር በተያያዘ በፈጸሙባችሁ ተንኮል የተነሳ አንገላተዋችኋል፤ ኮዝቢ ከፌጎር ጋር በተያያዘ የተከሰተው መቅሰፍት በመጣበት ዕለት+ የተገደለች የምድያማዊው አለቃ ልጅ ነች።”+