አራተኛ መጽሐፍ
(መዝሙር 90-106)
የእውነተኛው አምላክ ሰው የሙሴ ጸሎት።+
90 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መኖሪያችን ሆነሃል።+
2 ተራሮች ሳይወለዱ፣
ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ+ በፊት፣
ከዘላለም እስከ ዘላለም አንተ አምላክ ነህ።+
3 ሟች የሆነ ሰው ወደ አፈር እንዲመለስ ታደርጋለህ፤
“የሰው ልጆች ሆይ፣ ወደ አፈር ተመለሱ”+ ትላለህ።
4 በአንተ ዘንድ ሺህ ዓመት፣ እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣+
እንደ አንድ ክፍለ ሌሊትም ነው።
5 ጠራርገህ ታስወግዳቸዋለህ፤+ እንደ ሕልም ይጠፋሉ፤
በማለዳ ሲታዩ እንደሚለመልም ሣር ናቸው።+
6 ጠዋት ላይ ሣሩ ያቆጠቁጣል፤ ደግሞም ይለመልማል፤
ምሽት ላይ ግን ጠውልጎ ይደርቃል።+
7 በቁጣህ አልቀናልና፤+
ከታላቅ ቁጣህም የተነሳ ተሸብረናል።
8 በደላችንን በፊትህ ታኖራለህ፤+
የደበቅናቸው ነገሮች በፊትህ ብርሃን ተጋልጠዋል።+
9 ከኃይለኛ ቁጣህ የተነሳ ዘመናችን ይመናመናል፤
ዕድሜያችንም ሽው ብሎ ያልፋል።
10 የዕድሜያችን ርዝማኔ 70 ዓመት ነው፤
ለየት ያለ ጥንካሬ ካለን ደግሞ 80+ ዓመት ቢሆን ነው።
ይህም በችግርና በሐዘን የተሞላ ነው፤
ፈጥኖ ይነጉዳል፤ እኛም እናልፋለን።+
11 የቁጣህን ኃይል መረዳት የሚችል ማን ነው?
ቁጣህ፣ አንተ መፈራት የሚገባህን ያህል ታላቅ ነው።+
12 ጥበበኛ ልብ ማግኘት እንችል ዘንድ፣
ዕድሜያችንን እንዴት መቁጠር እንዳለብን አስተምረን።+
13 ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ!+ ይህ ሁኔታ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው?+
ለአገልጋዮችህ ራራላቸው።+
14 በሕይወት ዘመናችን ሁሉ እልል እንድንልና ሐሴት እንድናደርግ፣+
በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን አጥግበን።+
15 ባጎሳቆልከን ዘመን ልክ፣
መከራም ባየንባቸው ዓመታት መጠን+ ሐሴት እንዲሰማን አድርገን።+
16 አገልጋዮችህ ሥራህን ይዩ፤
ልጆቻቸውም ግርማህን ይመልከቱ።+
17 የአምላካችን የይሖዋ ሞገስ በእኛ ላይ ይሁን፤
የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።
አዎ፣ የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።+