ዘፍጥረት
10 የኖኅ ወንዶች ልጆች የሆኑት የሴም፣ የካም እና የያፌት ታሪክ ይህ ነው።
ከጥፋት ውኃ በኋላ ወንዶች ልጆች ወለዱ።+ 2 የያፌት ወንዶች ልጆች ጎሜር፣+ ማጎግ፣+ ማዳይ፣ ያዋን፣ ቱባል፣+ መሼቅ+ እና ቲራስ+ ነበሩ።
3 የጎሜር ወንዶች ልጆች አሽከናዝ፣+ ሪፋት እና ቶጋርማ+ ነበሩ።
4 የያዋን ወንዶች ልጆች ኤሊሻ፣+ ተርሴስ፣+ ኪቲም+ እና ዶዳኒም ነበሩ።
5 በደሴቶች ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች እንደየቋንቋቸውና እንደየቤተሰባቸው በየብሔራቸው በመሆን ወደየምድራቸው የተሰራጩት ከእነዚህ ነው።
6 የካም ወንዶች ልጆች ኩሽ፣ ሚጽራይም፣+ ፑጥ+ እና ከነአን+ ነበሩ።
7 የኩሽ ወንዶች ልጆች ሴባ፣+ ሃዊላ፣ ሳብታ፣ ራአማ+ እና ሳብተካ ነበሩ።
የራአማ ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን ነበሩ።
8 ኩሽ ናምሩድን ወለደ። እሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኃያል ሰው ነበር። 9 እሱም ይሖዋን የሚቃወም ኃያል አዳኝ ሆነ። በዚህም የተነሳ “እንደ ናምሩድ ያለ ይሖዋን የሚቃወም ኃያል አዳኝ” ይባል ነበር። 10 የግዛቱ መጀመሪያም* በሰናኦር+ ምድር የሚገኙት ባቤል፣+ ኤሬክ፣+ አካድ እና ካልኔ ነበሩ። 11 ከዚያ ምድር ተነስቶም ወደ አሦር+ በመሄድ ነነዌን፣+ ረሆቦትኢርን እና ካላህን ቆረቆረ፤ 12 እንዲሁም በነነዌና በካላህ መካከል የምትገኘውን ረሰንን ቆረቆረ፤ እሷም ታላቋ ከተማ ናት።*
13 ሚጽራይም ሉድን፣+ አናሚምን፣ ለሃቢምን፣ ናፊቱሂምን፣+ 14 ጳትሩሲምን፣+ ካስሉሂምን (ፍልስጤማውያን+ የተገኙት ከእሱ ነው) እንዲሁም ካፍቶሪምን+ ወለደ።
15 ከነአን የበኩር ልጁን ሲዶናን፣+ ሄትን+ 16 እንዲሁም ኢያቡሳዊውን፣+ አሞራዊውን፣+ ገርጌሻዊውን፣ 17 ሂዋዊውን፣+ አርቃዊውን፣ ሲናዊውን፣ 18 አርዋዳዊውን፣+ ጸማራዊውን እና ሃማታዊውን+ ወለደ። ከዚያ በኋላ የከነአናውያን ቤተሰቦች ተበተኑ። 19 በመሆኑም የከነአናውያን ወሰን ከሲዶና አንስቶ በጋዛ+ አቅራቢያ እስካለችው እስከ ጌራራ+ እንዲሁም እስከ ሰዶም፣ ገሞራ፣+ አድማህ እና በላሻ አቅራቢያ እስካለችው እስከ ጸቦይም+ ድረስ ያለው ነበር። 20 የካም ወንዶች ልጆች እንደየቤተሰባቸውና እንደየቋንቋቸው በየአገራቸውና በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ።
21 የኤቤር+ ወንዶች ልጆች ሁሉ ቅድመ አያትና የታላቅየው የያፌት ወንድም* የሆነው ሴምም ልጆች ወለደ። 22 የሴም ወንዶች ልጆች ኤላም፣+ አሹር፣+ አርፋክስድ፣+ ሉድ እና አራም+ ነበሩ።
23 የአራም ወንዶች ልጆች ዑጽ፣ ሁል፣ ጌተር እና ማሽ ነበሩ።
24 አርፋክስድ ሴሎምን+ ወለደ፤ ሴሎምም ኤቤርን ወለደ።
25 ኤቤር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የአንደኛው ስም ፋሌቅ*+ ነበር፤ ምክንያቱም በእሱ የሕይወት ዘመን ምድር ተከፋፍላ* ነበር። የወንድሙ ስም ደግሞ ዮቅጣን+ ነበር።
26 ዮቅጣን አልሞዳድን፣ ሸሌፍን፣ ሃጻርማዌትን፣ ያራህን፣+ 27 ሃዶራምን፣ ዑዛልን፣ ዲቅላን፣ 28 ኦባልን፣ አቢማዔልን፣ ሳባን፣ 29 ኦፊርን፣+ ሃዊላን እና ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ነበሩ።
30 መኖሪያ ስፍራቸውም ከሜሻ አንስቶ እስከ ሰፋር ይኸውም እስከ ምሥራቅ ተራራማ አካባቢ ድረስ ይዘልቃል።
31 የሴም ወንዶች ልጆች እንደየቤተሰባቸውና እንደየቋንቋቸው በየአገራቸውና በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ።+
32 የኖኅ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች እንደየዘር ሐረጋቸው በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውኃው በኋላ ብሔራት ሁሉ በምድር ላይ የተሰራጩት ከእነዚህ ነበር።+