መዝሙር
ማስኪል።* ዳዊት ዋሻ ውስጥ በነበረበት ጊዜ+ የዘመረው መዝሙር። ጸሎት።
142 ድምፄን አውጥቼ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ እጣራለሁ፤+
ሞገስ እንዲያሳየኝ ይሖዋን እማጸናለሁ።
በዚህ ጊዜ ጎዳናዬን ትመለከታለህ።+
በምሄድበት መንገድ ላይ
በስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ።
5 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጣራለሁ።
6 መንፈሴ እጅግ ተደቁሷልና፣
እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ።
ከእኔ ይልቅ ብርቱ ስለሆኑ
ከሚያሳድዱኝ ሰዎች ታደገኝ።+
7 ስምህን አወድስ ዘንድ
ከእስር ቤት አውጣኝ።*
ደግነት ስለምታሳየኝ
ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰብሰቡ።