ኤርምያስ
10 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይሖዋ በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ። 2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
3 የእነዚህ ሕዝቦች ልማድ ከንቱ* ነውና፤
ጉዳት ማድረስም ሆነ
ምንም ዓይነት መልካም ነገር መሥራት ስለማይችሉ አትፍሯቸው።”+
6 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+
አንተ ታላቅ ነህ፤ ስምህም ታላቅና ኃያል ነው።
7 የብሔራት ንጉሥ ሆይ፣+ አንተን የማይፈራ ማን ነው? አንተ ልትፈራ ይገባሃልና፤
ምክንያቱም ከብሔራት ጠቢባን ሁሉ እንዲሁም ከመንግሥቶቻቸው ሁሉ መካከል
እንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+
8 ሁሉም የማመዛዘን ችሎታ የጎደላቸውና ሞኞች ናቸው።+
ከእንጨት ምስል የሚመጣ መመሪያ ፈጽሞ ከንቱ* ነው።+
9 በእጅ ጥበብ ባለሙያና በአንጥረኛ የተሠራ
የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣+ ወርቅም ከዑፋዝ ይመጣል።
ልብሳቸው በሰማያዊ ክርና በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው።
ሁሉም በባለሙያዎች የተሠሩ ናቸው።
10 ይሖዋ ግን እውነተኛ አምላክ ነው።
ከቁጣው የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤+
የእሱን ውግዘት ሊቋቋም የሚችል አንድም ብሔር የለም።
11 * እናንተ እንዲህ በሏቸው፦
“ሰማያትንና ምድርን ያልሠሩት አማልክት
ከምድር ገጽ፣ ከእነዚህም ሰማያት በታች ይጠፋሉ።”+
14 እያንዳንዱ ሰው ማስተዋልና እውቀት የጎደለው ድርጊት ይፈጽማል።
የሚመረመሩበት ቀን ሲመጣ ይጠፋሉ።
ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+
17 አንቺ የተከበብሽ ሴት፣
ጓዝሽን ከመሬት ላይ ሰብስቢ።
18 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
ቁስሌ የማይድን ነው።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ ይህ የእኔ ሕመም ነው፤ ልሸከመውም ይገባል።
20 ድንኳኔ ፈርሷል፤ የድንኳኔም ገመዶች ሁሉ ተበጥሰዋል።+
ወንዶች ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከዚህ በኋላ አይኖሩም።+
ድንኳኔን የሚተክልልኝ ወይም የድንኳኔን ሸራዎች የሚዘረጋልኝ አንድም ሰው የለም።
ማስተዋል የጎደለው ድርጊት የፈጸሙት ለዚህ ነው፤
መንጎቻቸውም ሁሉ ተበታትነዋል።”+
22 አዳምጡ! አንድ ወሬ ስሙ! ወደዚህ እየመጣ ነው!
23 ይሖዋ ሆይ፣ የሰው መንገድ በራሱ እጅ እንዳልሆነ በሚገባ አውቃለሁ።
አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም።+
25 አንተን ችላ በሚሉ ብሔራት+
እንዲሁም ስምህን በማይጠሩ ነገዶች ላይ ቁጣህን አፍስስ።