ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት መዝሙር።
61 አምላክ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ስማ።
ጸሎቴን በትኩረት አዳምጥ።+
2 ልቤ ተስፋ በቆረጠ ጊዜ
ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ።+
ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለ ዓለት ምራኝ።+
3 አንተ መጠጊያዬ ነህና፤
ከጠላት የምትጠብቀኝ ጽኑ ግንብ ነህ።+
4 በድንኳንህ ለዘላለም በእንግድነት እቀመጣለሁ፤+
በክንፎችህ ጥላ ሥር እጠለላለሁ።+ (ሴላ)
5 አምላክ ሆይ፣ ስእለቴን ሰምተሃልና።
ስምህን የሚፈሩትን ሰዎች ርስት ሰጥተኸኛል።+
6 የንጉሡን ሕይወት ታረዝምለታለህ፤+
ዕድሜውም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይሆናል።
7 በአምላክ ፊት ለዘላለም ይነግሣል፤+
ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት እንዲጠብቁት እዘዝ።+
8 እኔም ስእለቴን በየቀኑ ስፈጽም፣+
ለስምህ ለዘላለም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+