25 ሹሃዊው በልዳዶስ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “የመግዛት ሥልጣንና አስፈሪ ኃይል የእሱ ነው፤
በሰማይ ሰላምን ያሰፍናል።
3 የሠራዊቱ ብዛት ሊቆጠር ይችላል?
የእሱ ብርሃን የማያበራበት ማን አለ?
4 ታዲያ ሟች የሆነ ሰው በአምላክ ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል?+
ወይስ ከሴት የተወለደ ሰው እንዴት ንጹሕ ሊሆን ይችላል?+
5 ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለችም፤
ከዋክብትም በእሱ ፊት ንጹሕ አይደሉም፤
6 እጭ የሆነው ሟች የሰው ልጅ፣
ትል የሆነው ሰውማ ምንኛ የባሰ ይሆን!”