137 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣+ በዚያ ተቀምጠን ነበር።
ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።+
2 በመካከሏ በሚገኙ የአኻያ ዛፎች ላይ
በገናዎቻችንን ሰቀልን።+
3 የማረኩን ሰዎች በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤+
የሚያፌዙብን ሰዎች በመዝሙር እንድናዝናናቸው
“ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።
4 የይሖዋን መዝሙር
በባዕድ ምድር እንዴት ልንዘምር እንችላለን?
5 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺን ብረሳ፣
ቀኝ እጄ ትክዳኝ።+
6 ሳላስታውስሽ ብቀር፣
ኢየሩሳሌምን ለደስታዬ ምክንያት
ከሆኑት ነገሮች በላይ ባላደርግ፣+
ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ትጣበቅ።
7 ይሖዋ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን
ኤዶማውያን ያሉትን አስታውስ፤
“አፍርሷት! ከሥረ መሠረቷ አፍርሷት!”+ ብለው ነበር።
8 በቅርቡ የምትጠፊው አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣+
በእኛ ላይ በፈጸምሽው በዚያው ድርጊት
ብድራትሽን የሚመልስ ደስተኛ ይሆናል።+
9 ልጆችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥ+
ደስተኛ ይሆናል።