ኢሳይያስ
21 በምድረ በዳው ባሕር* ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+
ከደቡብ አቅጣጫ አውሎ ነፋሳት እየጠራረጉ እንደሚመጡ፣
ከምድረ በዳ ይኸውም አስፈሪ ከሆነው ምድር የሆነ ነገር እየመጣ ነው።+
2 አንድ የሚያስጨንቅ ራእይ ተነገረኝ፦
ከሃዲው ክህደት ይፈጽማል፤
አጥፊውም ያጠፋል።
ኤላም ሆይ፣ ተነሺ! ሜዶን ሆይ፣ ክበቢ!+
እሷ ያስከተለችው ሲቃ ሁሉ እንዲያከትም አደርጋለሁ።+
ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት፣
ምጥ ያዘኝ።
እጅግ ከመጨነቄ የተነሳ መስማት ተሳነኝ፤
እጅግ ከመረበሼም የተነሳ ማየት አቃተኝ።
4 ልቤ ደከመ፤ በፍርሃት ተንቀጠቀጥኩ።
የምናፍቀው የምሽት ድንግዝግዝታ ሽብር ለቀቀብኝ።
5 ማዕዱን አሰናዱ፤ መቀመጫ ቦታዎቹን አዘጋጁ!
ብሉ፣ ጠጡ!+
እናንተ መኳንንት፣ ተነሱ፤ ጋሻውን ዘይት ቀቡ!
6 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦
“ሂድ፣ ጠባቂ አቁም፤ የሚያየውንም ነገር እንዲናገር አድርግ።”
ዓይኑን ተክሎ በከፍተኛ ትኩረት ተመለከተ።
8 ከዚያም እንደ አንበሳ ጮኾ እንዲህ አለ፦
“ይሖዋ ሆይ፣ በየቀኑ በመጠበቂያው ግንብ ላይ ቆሜአለሁ፤
በየሌሊቱም በጥበቃ ቦታዬ ላይ ተሰይሜአለሁ።+
9 እየመጣ ያለውን ነገር ተመልከት፦
ሰዎች በፈረሶች በሚጎተት የጦር ሠረገላ እየመጡ ነው!”+
ከዚያም ጮክ ብሎ እንዲህ አለ፦
“ወደቀች! ባቢሎን ወደቀች!+
የተቀረጹትን የአማልክቷን ምስሎች በሙሉ መሬት ላይ ጥሎ ሰባበረ!”+
አንዱ ከሴይር ጠርቶኝ እንዲህ አለኝ፦+
“ጠባቂ ሆይ፣ ስለ ሌሊቱ ምን ትላለህ?
ጠባቂ ሆይ፣ ስለ ሌሊቱ ምን ትላለህ?”
12 ጠባቂውም እንዲህ አለ፦
“ሊነጋ ነው፤ ሆኖም ተመልሶ ይመሻል።
መጠየቅ ከፈለጋችሁ ጠይቁ።
ተመልሳችሁ ኑ!”
13 በበረሃማው ሜዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦
እናንተ የዴዳን+ ተጓዥ ነጋዴዎች ሆይ፣
በበረሃማው ሜዳ በሚገኘው ዱር ሌሊቱን ታሳልፋላችሁ።
15 እነሱ ከሰይፍ፣ ከተመዘዘ ሰይፍ፣
ከተደገነ ቀስትና ከተፋፋመ ጦርነት ሸሽተዋልና።
16 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛል፦ “እንደ ቅጥር ሠራተኛ የሥራ ዘመን፣* በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የቄዳር+ ክብር ሙሉ በሙሉ ይጠፋል። 17 ከቄዳር ተዋጊዎች የሚተርፉት ቀስተኞች ጥቂት ይሆናሉ፤ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይህን ተናግሯልና።”