ኢሳይያስ
አንቺም የይሖዋ አፍ በሚያወጣልሽ
አዲስ ስም ትጠሪያለሽ።+
3 በይሖዋ እጅ የውበት ዘውድ፣
በአምላክሽ መዳፍ የንጉሥ ጥምጥም ትሆኛለሽ።
ከዚህ ይልቅ “ደስታዬ በእሷ ነው” ተብለሽ ትጠሪያለሽ፤+
ምድርሽም “ያገባች ሴት” ትባላለች።
ይሖዋ በአንቺ ደስ ይለዋልና፤
ምድርሽም እንዳገባች ሴት ትሆናለች።
5 አንድ ወጣት ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣
ወንዶች ልጆችሽ አንቺን ያገባሉ።
አንድ ሙሽራ በሙሽራይቱ ሐሴት እንደሚያደርግ፣
አምላክሽም በአንቺ ሐሴት ያደርጋል።+
6 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ በቅጥሮችሽ ላይ ጠባቂዎች አቁሜአለሁ።
ቀኑንም ሆነ ሌሊቱን በሙሉ፣ መቼም ቢሆን ዝም ሊሉ አይገባም።
እናንተ ስለ ይሖዋ የምትናገሩ፣
ፈጽሞ አትረፉ፤
7 ደግሞም ኢየሩሳሌምን አጽንቶ እስኪመሠርታት፣
አዎ፣ የምድር ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ ምንም እረፍት አትስጡት።”+
8 ይሖዋ በቀኝ እጁ፣ ብርቱ በሆነውም ክንዱ እንዲህ ሲል ምሏል፦
“ከእንግዲህ እህልሽን ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤
የደከምሽበትንም አዲስ የወይን ጠጅ የባዕድ አገር ሰዎች አይጠጡትም።+
10 በበሮቹ በኩል እለፉ፤ እለፉ።
ለሕዝቡ መንገዱን ጥረጉ።+
ሥሩ፤ አውራ ጎዳናውን ሥሩ።
ድንጋዮቹን አስወግዱ።+
11 እነሆ፣ ይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ አውጇል፦
“ለጽዮን ሴት ልጅ
‘እነሆ፣ መዳንሽ ቀርቧል።+
እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤
የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ’ በሏት።”+