መዝሙር
2 ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?”
ለምን ይበሉ?+
3 አምላካችን ያለው በሰማያት ነው፤
እሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።
4 የእነሱ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣
የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+
5 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+
ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤
6 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም፤
አፍንጫ አላቸው፤ ማሽተት ግን አይችሉም፤
7 እጅ አላቸው፤ መዳሰስ ግን አይችሉም፤
እግር አላቸው፤ መራመድ ግን አይችሉም፤+
በጉሮሯቸው የሚያሰሙት ድምፅ የለም።+
8 የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣
እንደ እነሱ ይሆናሉ።+
10 የአሮን ቤት ሆይ፣+ በይሖዋ ታመኑ፤
እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።
13 ይሖዋ እሱን የሚፈሩትን፣
ታናናሾችንም ሆነ ታላላቆችን ይባርካል።
18 እኛ ግን ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣
ያህን እናወድሳለን።
ያህን አወድሱ!*