መዝሙር
የዳዊት መዝሙር።
3 ይሖዋ ሆይ፣ ታስተውለው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ቦታ ትሰጠውስ ዘንድ ሟች የሆነው የሰው ልጅ ምንድን ነው?+
7 እጆችህን ከላይ ዘርጋ፤
ከሚያጥለቀልቅ ውኃ ታደገኝ፤ ደግሞም አድነኝ፤
8 እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤
ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ።*
9 አምላክ ሆይ፣ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+
11 ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም፤
እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤
ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ።
12 ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻችን በፍጥነት እንደሚያድጉ ችግኞች፣
ሴቶች ልጆቻችን ደግሞ ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደተቀረጹ የማዕዘን ዓምዶች ይሆናሉ።
13 ጎተራዎቻችን በልዩ ልዩ የእህል ዓይነቶች ጢም ብለው ይሞላሉ፤
በመስክ ያሉት መንጎቻችን ተራብተው ሺዎች ደግሞም አሥር ሺዎች ይሆናሉ።
14 የከበዱት ከብቶቻችን ጉዳት አይደርስባቸውም ወይም አይጨነግፉም፤
በአደባባዮቻችን ላይ የጭንቅ ዋይታ አይሰማም።
15 ይህ የሚሆንለት ሕዝብ ደስተኛ ነው!
አምላኩ ይሖዋ የሆነለት ሕዝብ ደስተኛ ነው!+