ኢዮብ
36 ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2 “አምላክን ወክዬ ገና የምናገረው ነገር ስላለ
ጉዳዩን በማብራራበት ጊዜ ትንሽ ታገሠኝ።
3 ስለማውቀው ነገር በሰፊው እናገራለሁ፤
ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደሆነም አስታውቃለሁ።+
4 በእርግጥ የምናገረው ቃል ውሸት አይደለም፤
እውቀቱ ፍጹም የሆነው አምላክ+ በፊትህ ነው።
8 ይሁንና ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣
በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣
9 ከመታበያቸው የተነሳ ስለፈጸሙት ድርጊት
ይኸውም ስለ በደላቸው ይነግራቸዋል።
10 እርማት እንዲቀበሉ ጆሯቸውን ይከፍታል፤
ከክፋትም እንዲመለሱ ይነግራቸዋል።+
13 በልባቸው አምላክ የለሽ* የሆኑ ቂም ይይዛሉ።
እሱ በሚያስራቸው ጊዜም እንኳ እርዳታ ለማግኘት አይጮኹም።
15 ሆኖም አምላክ* የተጎሳቆሉ ሰዎችን ከጉስቁልናቸው ይታደጋቸዋል፤
ጭቆና በሚደርስባቸው ጊዜ ጆሯቸውን ይከፍታል።
17 ፍርድ ሲበየንና ፍትሕ ሲሰፍን፣
በክፉዎች ላይ በሚፈጸመው ፍርድ ትረካለህ።+
19 እርዳታ ለማግኘት መጮኽህ፣
ወይም የምታደርገው ማንኛውም ብርቱ ጥረት ከጭንቀት ነፃ ያደርግሃል?+
20 ሰዎች ካሉበት ስፍራ የሚጠፉበትን
የሌሊቱን ጊዜ አትናፍቅ።
21 ከጉስቁልና ይልቅ ይህን መርጠህ፣+
ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
22 እነሆ፣ አምላክ በኃይሉ ከፍ ከፍ ብሏል፤
እንደ እሱ ያለ አስተማሪ ማን ነው?
25 የሰው ልጆች ሁሉ አይተውታል፤
ሟች የሆነ ሰው ከሩቅ ያያል።
29 የደመናትን ንብርብር፣
ከድንኳኑም የሚሰማውን ነጎድጓድ+ ማን ሊያስተውል ይችላል?
32 በእጆቹ መብረቁን ይሸፍናል፤
ወደ ዒላማውም ይሰደዋል።+
33 ነጎድጓዱ ስለ እሱ ይናገራል፤
ከብቶች እንኳ ሳይቀሩ ማን* እየመጣ እንዳለ ይጠቁማሉ።