ኤርምያስ
30 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ 2 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የምነግርህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው። 3 “እነሆ፣ ተማርከው የተወሰዱትን ሕዝቤን፣ እስራኤልንና ይሁዳን የምሰበስብበት ጊዜ ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ለአባቶቻቸው ወደሰጠኋት ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ዳግመኛ ይወርሷታል” ይላል ይሖዋ።’”+
4 ይሖዋ ለእስራኤልና ለይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው።
5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“የሚንቀጠቀጡ ሰዎችን ድምፅ ሰምተናል፤
ሽብር ነግሦአል፤ ሰላምም የለም።
6 ወንድ፣ መውለድ ይችል እንደሆነ እስቲ ጠይቁ።
የሰዉ ሁሉ ፊት የገረጣው ለምንድን ነው?
በዓይነቱ ልዩ የሆነ ቀን ነው፤
ለያዕቆብ የጭንቅ ጊዜ ይሆናል።
ሆኖም ከዚያ ቀን ይተርፋል።”
8 “በዚያም ቀን፣” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “ቀንበሩን ከአንገትህ ላይ እሰብራለሁ፤ ማሰሪያህንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህ እንግዶች* ባሪያቸው አያደርጉትም።* 9 እነሱም አምላካቸውን ይሖዋንና የማስነሳላቸውን ንጉሣቸውን ዳዊትን ያገለግላሉ።”+
10 “አንተም አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ” ይላል ይሖዋ፤
“እስራኤል ሆይ፣ አትሸበር።+
አንተን ከሩቅ አገር፣
ዘርህንም ተማርኮ ከተወሰደበት ምድር እታደጋለሁና።+
ያዕቆብ ይመለሳል፤ ሳይረበሽም ተረጋግቶ ይቀመጣል፤
የሚያስፈራቸው አይኖርም።”+
11 “እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ።
12 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
“ስብራትሽ ፈውስ የለውም።+
ቁስልሽ የማይድን ነው።
13 የሚሟገትልሽ የለም፤
ቁስልሽ በምንም መንገድ ሊድን አይችልም።
ለአንቺ የሚሆን ፈውስ የለም።
14 አጥብቀው የሚወዱሽ ሁሉ ረስተውሻል።+
ከእንግዲህ አይፈልጉሽም።
15 ከስብራትሽ የተነሳ የምትጮኺው ለምንድን ነው?
ሕመምሽ የማይፈወስ ሆኗል!
ከባድ በደል ስለፈጸምሽና ብዙ ኃጢአት ስለሠራሽ+
ይህን አድርጌብሻለሁ።
የሚዘርፉሽ ሁሉ ይዘረፋሉ፤
የሚበዘብዙሽንም ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።”+
17 “ይሁንና ጤንነትሽን እመልስልሻለሁ፤ ቁስሎችሽንም እፈውሳለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤
“እነሱ ግን የተገለለች፣
‘ማንም የማይፈልጋት ጽዮን’ ብለውሻል።”+
18 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፣ ከያዕቆብ ድንኳኖች የተማረኩትን እሰበስባለሁ፤+
ለማደሪያ ድንኳኖቹም እራራለሁ።
ከተማዋ በጉብታዋ ላይ ዳግም ትገነባለች፤+
የማይደፈረውም ማማ በተገቢው ቦታ ላይ ይቆማል።
19 ከእነሱም የምስጋናና የሳቅ ድምፅ ይሰማል።+
20 ወንዶች ልጆቹ እንደቀድሞው ጊዜ ይሆናሉ፤
ጉባኤውም በፊቴ ጸንቶ ይመሠረታል።+
እሱን በሚጨቁኑት ሁሉ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ።+
21 ታላቅ ግርማ የተላበሰው መሪ ከራሱ ወገን ይገኛል፤
ገዢውም ከመካከሉ ይወጣል።
ወደ እኔ እንዲቀርብ እፈቅድለታለሁ፤ እሱም ወደ እኔ ይቀርባል።”
“አለዚያ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር* ማን ነው?” ይላል ይሖዋ።
22 “እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤+ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።”+
23 እነሆ፣ የይሖዋ አውሎ ነፋስ በታላቅ ቁጣ ይነሳል፤+
በክፉዎች ራስ ላይ እየተሽከረከረ የሚወርድ ኃይለኛ ነፋስ ይነፍሳል።
24 ይሖዋ የልቡን ሐሳብ ሳያከናውንና ሳይፈጽም፣
የሚነደው ቁጣው አይመለስም።+
በዘመኑ መጨረሻ ይህን ትረዳላችሁ።+