አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ማቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት የማቴዎስ ወንጌል የመጽሐፉ ይዘት 1 የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ (1-17) ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሁኔታ (18-25) 2 ኮከብ ቆጣሪዎች መጡ (1-12) ወደ ግብፅ መሸሽ (13-15) ሄሮድስ ወንዶች ልጆችን ገደለ (16-18) ወደ ናዝሬት ተመለሱ (19-23) 3 መጥምቁ ዮሐንስ ሰበከ (1-12) ኢየሱስ ተጠመቀ (13-17) 4 ዲያብሎስ ኢየሱስን ፈተነው (1-11) ኢየሱስ በገሊላ መስበክ ጀመረ (12-17) የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ተጠሩ (18-22) ኢየሱስ ሰበከ፣ አስተማረ እንዲሁም ፈወሰ (23-25) 5 የተራራው ስብከት (1-48) ኢየሱስ በተራራ ላይ ማስተማር ጀመረ (1, 2) ለደስታ ምክንያት የሚሆኑ ዘጠኝ ነገሮች (3-12) ጨውና ብርሃን (13-16) ኢየሱስ ሕጉን ሊፈጽም መጣ (17-20) ቁጣን (21-26)፣ ምንዝርን (27-30)፣ ፍቺን (31, 32)፣ ቃለ መሐላን (33-37)፣ አጸፋ መመለስን (38-42)፣ ጠላትን መውደድን በተመለከተ የተሰጠ ምክር (43-48) 6 የተራራው ስብከት (1-34) “ግብዞች አትሁኑ” (1-4) ጸሎትን በተመለከተ የተሰጠ ትምህርት (5-15) የጸሎት ናሙና (9-13) ጾም (16-18) በምድር ሳይሆን በሰማይ ሀብት ማከማቸት (19-24) አትጨነቁ (25-34) የአምላክን መንግሥት ፈልጉ (33) 7 የተራራው ስብከት (1-27) “በሌሎች ላይ አትፍረዱ” (1-6) ደጋግማችሁ ለምኑ፣ ፈልጉ፣ አንኳኩ (7-11) ወርቃማው ሕግ (12) ጠባቡ በር (13, 14) “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” (15-23) በዓለት ላይና በአሸዋ ላይ የተሠራ ቤት (24-27) ሕዝቡ በኢየሱስ ትምህርት ተደነቁ (28, 29) 8 በሥጋ ደዌ የተያዘ ሰው ተፈወሰ (1-4) አንድ የጦር መኮንን ያሳየው እምነት (5-13) ኢየሱስ በቅፍርናሆም ብዙ ሰዎችን ፈወሰ (14-17) ኢየሱስን መከተል (18-22) ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አሰኘ (23-27) ኢየሱስ አጋንንቱን ወደ አሳማዎች እንዲገቡ ፈቀደላቸው (28-34) 9 ኢየሱስ አንድ ሽባ ፈወሰ (1-8) ኢየሱስ ማቴዎስን ጠራው (9-13) ጾምን በተመለከተ የቀረበ ጥያቄ (14-17) የኢያኢሮስ ሴት ልጅ፤ አንዲት ሴት የኢየሱስን ልብስ ነካች (18-26) ኢየሱስ ዓይነ ስውሮችንና ዱዳ የሆነውን ሰው ፈወሰ (27-34) አዝመራው ብዙ፣ ሠራተኞቹ ግን ጥቂት (35-38) 10 የኢየሱስ 12 ሐዋርያት (1-4) አገልግሎትን በተመለከተ የተሰጠ መመሪያ (5-15) ደቀ መዛሙርቱ ስደት ይደርስባቸዋል (16-25) ሰውን ሳይሆን አምላክን ፍሩ (26-31) ሰላምን ሳይሆን ሰይፍን አመጣለሁ (32-39) የኢየሱስን ደቀ መዛሙርት መቀበል (40-42) 11 መጥምቁ ዮሐንስ ተወደሰ (1-15) ዓመፀኛው ትውልድ ተወገዘ (16-24) ‘ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለልጆች ገለጥክላቸው’ (25-27) የኢየሱስ ቀንበር እረፍት ይሰጣል (28-30) 12 ኢየሱስ “የሰንበት ጌታ ነው” (1-8) እጁ የሰለለ አንድ ሰው ተፈወሰ (9-14) አምላክ የሚወደው አገልጋይ (15-21) ኢየሱስ በአምላክ ኃይል አጋንንትን አስወጣ (22-30) ይቅር የማይባል ኃጢአት (31, 32) ዛፍ በፍሬው ይታወቃል (33-37) የዮናስ ምልክት (38-42) ሰባት ርኩስ መናፍስት ይዞ ይመጣል (43-45) የኢየሱስ እናትና ወንድሞች (46-50) 13 የመንግሥቱ ምሳሌዎች (1-52) ዘሪው (1-9) ኢየሱስ ምሳሌዎችን የተጠቀመበት ምክንያት (10-17) የዘሪው ምሳሌ ትርጉም (18-23) ስንዴውና እንክርዳዱ (24-30) የሰናፍጭ ዘርና እርሾ (31-33) “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ” (34, 35) የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ ትርጉም (36-43) የተደበቀ ውድ ሀብትና ዕንቁ (44-46) መረቡ (47-50) አዲስና አሮጌ ዕቃ የያዘ የከበረ ሀብት ማከማቻ (51, 52) ኢየሱስን የአገሩ ሰዎች አልተቀበሉትም (53-58) 14 የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ተቆረጠ (1-12) ኢየሱስ 5,000 ሰዎችን መገበ (13-21) ኢየሱስ በውኃ ላይ ተራመደ (22-33) በጌንሴሬጥ የተከናወነ ፈውስ (34-36) 15 “ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ቃል ሽራችኋል” (1-9) ሰውን የሚያረክሰው ከልብ የሚወጣ ነው (10-20) አንዲት ፊንቄያዊት ታላቅ እምነት አሳየች (21-28) ኢየሱስ የተለያዩ በሽታዎችን ፈወሰ (29-31) ኢየሱስ 4,000 ሰዎችን መገበ (32-39) 16 ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁ (1-4) “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠበቁ” (5-12) ‘የመንግሥተ ሰማያት ቁልፎች’ (13-20) “በዚህች ዓለት ላይ ጉባኤዬን እገነባለሁ” (18) ኢየሱስ እንደሚሞት ተናገረ (21-23) እውነተኛ ደቀ መዝሙር (24-28) 17 ኢየሱስ በተአምራዊ ሁኔታ ተለወጠ (1-13) “የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክል እምነት” (14-21) ኢየሱስ እንደሚሞት በድጋሚ ተናገረ (22, 23) ከዓሣ አፍ በተገኘው ሳንቲም ግብር ተከፈለ (24-27) 18 “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው” (1-6) ማሰናከያ (7-11) የጠፋው በግ ምሳሌ (12-14) “ወንድምህን ታተርፋለህ” (15-20) ይቅር ያላለው ባሪያ ምሳሌ (21-35) 19 ጋብቻና ፍቺ (1-9) የነጠላነት ስጦታ (10-12) ኢየሱስ ልጆችን ባረከ (13-15) ሀብታም የሆነ አንድ ወጣት ያቀረበው ጥያቄ (16-24) ለመንግሥቱ ሲባል መሥዋዕትነት መክፈል (25-30) 20 የወይን እርሻ ሠራተኞችና የተቀበሉት ክፍያ (1-16) ኢየሱስ እንደሚሞት በድጋሚ ተናገረ (17-19) በአምላክ መንግሥት ከፍ ያለ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠየቁ (20-28) ኢየሱስ የመጣው ለብዙዎች ቤዛ ሊሆን ነው (28) ሁለት ዓይነ ስውሮች ተፈወሱ (29-34) 21 ኢየሱስ እንደ ድል አድራጊ ሆኖ ገባ (1-11) ኢየሱስ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደሱ አባረረ (12-17) የበለስ ዛፏ ተረገመች (18-22) የኢየሱስን ሥልጣን ተገዳደሩ (23-27) የሁለቱ ልጆች ምሳሌ (28-32) ነፍሰ ገዳይ የሆኑት ገበሬዎች ምሳሌ (33-46) የማዕዘን ራስ ድንጋይ ተናቀ (42) 22 የሠርጉ ድግስ ምሳሌ (1-14) ‘የቄሳርን ለቄሳር፣ የአምላክን ለአምላክ’ (15-22) ትንሣኤን በተመለከተ የቀረበ ጥያቄ (23-33) ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት (34-40) ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው? (41-46) 23 የጸሐፍትንና የፈሪሳውያንን አርዓያ አትከተሉ (1-12) ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወዮላቸው! (13-36) ኢየሱስ ስለ ኢየሩሳሌም የተሰማውን ሐዘን ገለጸ (37-39) 24 የክርስቶስ መገኘት ምልክት (1-51) ጦርነት፣ የምግብ እጥረት፣ የምድር ነውጥ (7) ምሥራቹ ይሰበካል (14) “ታላቅ መከራ” (21, 22) የሰው ልጅ ምልክት (30) የበለስ ዛፍ (32-34) እንደ ኖኅ ዘመን (37-39) “ነቅታችሁ ጠብቁ” (42-44) ታማኙ ባሪያና ክፉው ባሪያ (45-51) 25 የክርስቶስ መገኘት ምልክት (1-46) የአሥሩ ደናግል ምሳሌ (1-13) የታላንቱ ምሳሌ (14-30) በጎችና ፍየሎች (31-46) 26 ካህናት ኢየሱስን ለመግደል አሴሩ (1-5) አንዲት ሴት ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት በኢየሱስ ላይ አፈሰሰች (6-13) የመጨረሻው ፋሲካና ይሁዳ የፈጸመው ክህደት (14-25) የጌታ ራት ተቋቋመ (26-30) ኢየሱስ፣ ጴጥሮስ እንደሚክደው ተናገረ (31-35) ኢየሱስ በጌትሴማኒ ጸለየ (36-46) ኢየሱስ ተያዘ (47-56) በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት ለፍርድ ቀረበ (57-68) ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው (69-75) 27 ኢየሱስ ለጲላጦስ አልፎ ተሰጠ (1, 2) ይሁዳ ታንቆ ሞተ (3-10) ኢየሱስ ጲላጦስ ፊት ቀረበ (11-26) ሰዎች አፌዙበት (27-31) በጎልጎታ በእንጨት ላይ ተቸነከረ (32-44) ኢየሱስ ሞተ (45-56) ኢየሱስ ተቀበረ (57-61) መቃብሩ እንዲጠበቅ አደረጉ (62-66) 28 ኢየሱስ ከሞት ተነሳ (1-10) ወታደሮቹ እንዲዋሹ ጉቦ ተሰጣቸው (11-15) ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ ተልእኮ ተሰጣቸው (16-20)