አርዓያ የሚሆኑ ሰዎች—ሊዲያ
ሊዲያ ክርስትናን የተቀበለችው በቅርቡ ቢሆንም በራሷ ተነሳሽነት ጳውሎስና ጓደኞቹን በእንግድነት ተቀብላቸዋለች። (የሐዋርያት ሥራ 16:14, 15) ይህንንም በማድረጓ ከእነዚህ ደቀ መዛሙርት ጋር ጊዜ የማሳለፍ ልዩ አጋጣሚ አግኝታለች። ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤት ሲለቀቁ ወዴት የሄዱ ይመስልሃል? በቀጥታ ያመሩት ወደ ሊዲያ ቤት ነው!—የሐዋርያት ሥራ 16:40
አንተስ እንደ ሊዲያ ቅድሚያውን ወስደህ ሌሎችን ይበልጥ ለማወቅ ጥረት ማድረግ ትችላለህ? ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? ቀላል በሚመስሉ ነገሮች ጀምር። በአንድ ጊዜ አንድ ሰው ብቻ በማነጋገር መጀመር ትችላለህ። በክርስቲያናዊ ስብሰባ ላይ በተገኘህ ቁጥር ቢያንስ ከአንድ ሰው ጋር ለመጨዋወት ግብ ልታወጣ ትችላለህ። በፈገግታ ለመቅረብ ሞክር። ምን እንደምታወራ ግራ ከገባህ ጥያቄ መጠየቅ ወይም ስለ ራስህ አንድ ነገር መናገር ትችላለህ። ጥሩ አዳማጭ ሁን። ቀስ በቀስ ማውራት እየቀለለህ ይመጣል። የምንናገራቸው ቃላት ከልብ የመነጩ ከሆኑ እንዲሁም ደግነት በተንጸባረቀበትና ደስ በሚል መንገድ ከተናገርን ብዙውን ጊዜ ሰዎች ጥሩ ምላሽ ይሰጡናል። (ምሳሌ 16:24) ሊዲያ ሰዎችን የምትወድና እንግዳ ተቀባይ ስለነበረች ጥሩ ጓደኞች ማፍራት ችላለች። አንተም የእሷን ምሳሌ ከተከተልክ ጥሩ ጓደኞች ይኖሩሃል!