መዝሙር 42
የአምላክ አገልጋይ ጸሎት
በወረቀት የሚታተመው
1. ሉዓላዊው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣
ክቡር ስምህ የተቀደሰ ይሁን።
ሁሉን ቻይ ነህ፤ ምን ይሳንሃል?
ስለ መንግሥትህ እንጸልያለን።
ያንተ መንግሥት ይምጣልን፤
በረከት ያፍስስልን።
2. አባታችን፣ ምስጋና ይድረስህ፤
ደግነትህ፣ ብዙ ነው በረከትህ።
ሕይወትን፣ ብርሃንን ፈጥረሃል፤
ጥበብ፣ ማስተዋል ካንተ ይገኛል።
ይገባሃል ውዳሴ፤
’ናመስግንህ ሁልጊዜ።
3. የዚህ ዓለም መከራው ብዙ ነው፤
መጽናኛ ግን ካንተ ነው ’ምናገኘው።
ሸክማችንን ተቀበለን፤
ጥንካሬ፣ ድፍረት ’ባክህ ስጠን።
ታማኝ እንድንሆን እርዳን፤
ልመናችንን ስማን።
(በተጨማሪም መዝ. 36:9፤ 50:14ን፣ ዮሐ. 16:33ን እና ያዕ. 1:5ን ተመልከት።)