መዝሙር 144
ዓይንህ ሽልማቱ ላይ ያተኩር!
በወረቀት የሚታተመው
1. ማየት፣ መስማት የተሳናቸው
ሲፈወሱ ይታይህ ደስታው!
የሕፃናት ሳቅ ሲያስተጋባ፣
የትም ሲያብብ ሰላም ደስታ፣
ሙታን ሲወጡ ከመቃብር፣
ኃጢያት፣ ዓመፅ ጠፍቶ ከምድር፣
(አዝማች)
ተስፋው ላይ ካተኮረ ዓይንህ፣
በዚህ ጊዜ ትኖራለህ።
2. ተኩላ ከጠቦት ጋር ይውላል፤
ጥጃ ከድብ ጋር ይሰማራል።
ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል፤
እነሱም ይታዘዙታል።
ታሪክ ሲሆን እንባና ለቅሶ፣
ሥቃይ፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት ተረስቶ፣
(አዝማች)
ተስፋው ላይ ካተኮረ ዓይንህ፣
በዚህ ጊዜ ትኖራለህ።
(በተጨማሪም ኢሳ. 11:6-9፤ 35:5-7ን እና ዮሐ. 11:24ን ተመልከት።)