ጥናት 4
ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ
ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
ጥቅሱን የምታነብበትን ዓላማ ቆም ብለህ አስብ። አድማጮችህ ከጥቅሱ ላይ ልታጎላው የፈለግከውን ነጥብ እንዲያስተውሉ በሚረዳ መንገድ ጥቅሱን አስተዋውቅ።
መጽሐፍ ቅዱስን ዋነኛ ማስረጃ አድርገህ ጥቀስ። በአምላክ መኖር ለሚያምኑ ሰዎች በምትናገርበት ጊዜ የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እርዳቸው፤ ይህን ማድረግህ ከሁሉ የላቀ ጥበብ የያዘውን የአምላክን ቃል እንደምታስተምር ያሳያል።
አድማጮችህ ጥቅሱ ምን እንደሚል ለማወቅ እንዲጓጉ አድርግ። ጥያቄ ከጠየቅክ አሊያም አንድ ችግር ከጠቀስክ በኋላ መልሱ ወይም መፍትሔው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሚገኝ ተናገር፤ አሊያም ደግሞ ለአንድ መሠረታዊ ሥርዓት ምሳሌ የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ጥቀስ።