ክፍል 3 ክለሳ
ከአስተማሪህ ጋር በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ምሳሌ 27:11ን አንብቡ።
ለይሖዋ ታማኝ እንድትሆን የሚያነሳሳህ ምንድን ነው?
(ምዕራፍ 34ን ተመልከት።)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀጥተኛ መመሪያ በማይኖርበት ጊዜ ጥሩ ውሳኔ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
(ምዕራፍ 35ን ተመልከት።)
በሁሉም ነገር ሐቀኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?
(ምዕራፍ 36ን ተመልከት።)
ማቴዎስ 6:33ን አንብቡ።
ከሥራና ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ምንጊዜም ‘ከሁሉ አስቀድመህ የአምላክን መንግሥት እንደምትፈልግ’ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
(ምዕራፍ 37ን ተመልከት።)
ልክ እንደ ይሖዋ ለሕይወት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ማሳየት የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
(ምዕራፍ 38ን ተመልከት።)
የሐዋርያት ሥራ 15:29ን አንብቡ።
ይሖዋ ከደም ጋር በተያያዘ የሰጠውን ትእዛዝ እንደምታከብር ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
የይሖዋ ትእዛዝ ምክንያታዊ እንደሆነ ይሰማሃል?
(ምዕራፍ 39ን ተመልከት።)
ሁለተኛ ቆሮንቶስ 7:1ን አንብቡ።
አካላዊና ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናን መጠበቅ ምን ነገሮችን ያካትታል?
(ምዕራፍ 40ን ተመልከት።)
አንደኛ ቆሮንቶስ 6:9, 10ን አንብቡ።
መጽሐፍ ቅዱስ የፆታ ግንኙነትን በተመለከተ ምን ይላል? አንተ ከዚህ ሐሳብ ጋር ትስማማለህ?
መጽሐፍ ቅዱስ የአልኮል መጠጥን በተመለከተ ምን መመሪያ ይዟል?
ማቴዎስ 19:4-6, 9ን አንብቡ።
አምላክ ትዳርን በተመለከተ ምን መመሪያ ሰጥቷል?
ጋብቻንና ፍቺን ሕጋዊ በሆነ መንገድ ማስመዝገብ ያለብን ለምንድን ነው?
(ምዕራፍ 42ን ተመልከት።)
ይሖዋ የማይደሰትባቸው አንዳንድ በዓላት የትኞቹ ናቸው? ለምንስ?
(ምዕራፍ 44ን ተመልከት።)
ዮሐንስ 17:16ን እና የሐዋርያት ሥራ 5:29ን አንብቡ።
ገለልተኛ እንደሆንክ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
የሰዎች ሕግ ከአምላክ ሕግ ጋር በሚጋጭበት ጊዜ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?
(ምዕራፍ 45ን ተመልከት።)
ማርቆስ 12:30ን አንብቡ።
ይሖዋን እንደምትወደው ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?