የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት
የአምላክ ስም ከነቀፋ ነጻ ሆነ
የአምላክ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- “ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፣ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፣ በሚጐበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።” (1 ጴጥሮስ 2:12) ስለዚህ እውነተኛ ክርስቲያኖች በይሖዋ ስም ላይ ነቀፋ ላለማምጣት መልካም የአኗኗር ዘይቤ ለመከተል ይጥራሉ።
ከዛምቢያ ራቅ ብሎ በሚገኝ ሰናንጋ በተባለ ክልል ውስጥ የሚኖር አንድ መምህር ከቤቱ ራዲዮ ይሰረቅበታል። በሚኖርበት አካባቢ የይሖዋ ምሥክሮች ይሰብኩ ስለነበር እነርሱን በስርቆት ወንጀል ከሰሳቸው። ራዲዮኔን ሰርቀውኛል በማለት ለፖሊስ አሳወቀ። ምሥክሮቹ ቤቱ ገብተው እንደነበር ለማስረዳት በወለሉ ላይ ያገኘውን ትራክት እንደ ማስረጃ አድርጎ አቀረበ። ሆኖም ፖሊሶቹ የሚናገረውን ከማመን ይልቅ ተመልሶ ቤቱን በደንብ እንዲፈትሽ መከሩት።
በዕለቱ በመምህሩ መኖሪያ አካባቢ ይሰብኩ የነበሩት ምሥክሮች መምህሩን ሄደው እንዲያነጋግሩ የሽማግሌዎች አካል አበረታታቸው። የተወሰኑት ወንድሞች ሄዱና የይሖዋን ስም ከነቀፋ ነጻ ለማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸው አነጋገሩት። በውይይታቸውም መሐል ቤቱ ውስጥ አንድ ልጅ እንዳገኙና ትራክትም እንደሰጡት ገለጹ። መምህሩ ምሥክሮቹ በሰጡት መግለጫ መሠረት ልጁ ማን እንደሆነ አወቀ። እንዲያውም፣ ልጁና መምህሩ የአንድ እምነት ተከታዮች ናቸው። መምህሩ ሄዶ ቢያነጋግረውም ልጁ ግን ካደ። ሆኖም መምህሩ የልጁን ቤተሰቦች አነጋግሮ ወደ ቤቱ በተመለሰ አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የልጁ እናት የተሰረቀውን ራዲዮ ይዘው መጡ።
መምህሩ የሐሰት ክስ በመመስረቱ በጣም እንደተጸጸተ በመግለጽ የሽማግሌዎችን አካል ይቅርታ ጠየቀ። ሽማግሌዎቹ ይቅርታ እንዳደረጉለት ከገለጹ በኋላ ምሥክሮቹ ከክሱ ነጻ መሆናቸውን ሁሉም ሰው እንዲያውቅ የምርመራው ውጤት ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ጠየቁት። የይሖዋን ስም ከነቀፋ ነጻ የሚያደርግ ማስታወቂያ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ተነገረ። የይሖዋ ምሥክሮች በአካባቢው በነጻነት መስበካቸውን መቀጠል ይችላሉ።
[በገጽ 19 ላይ የሚገኝ ካርታ/ሥዕል]
(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)
አፍሪካ
ዛምቢያ
[ምንጭ]
Mountain High Maps® Copyright © 1997 Digital Wisdom, Inc.