ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ሰኔ፦ ታላቁ ሰው (እንግሊዝኛ)፤ ለዘላለም መኖር (አማርኛ)፤ እውቀት (ትግርኛ) ሐምሌና ነሐሴ፦ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይኖርብሃልን? የሙታን መናፍስት— ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊ ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው— እንዴት ልታገኘው ትችላለህ? (እንግሊዝኛ) እንዲሁም የምትወዱት ሰው ሲሞት። መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ ወይም የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው።
◼ ሰኔ 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የሚጣለው ቀረጥ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ የሚቀጥለው ዓመት የቀን መቁጠሪያ ዋጋ ወደፊት ይገለጻል።
◼ በባሕር ማዶ ላሉ የአማርኛና የትግርኛ ተናጋሪ ጉባኤዎች የመጠበቂያ ግንብ ቅጂዎችን በተፋጠነ መልኩ ለማድረስ እንዲቻል ትንሽ ጥቅል ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆኑ ወደ አውሮፓ ወይም አሜሪካ የሚጓዙ ወንድሞች ወይም እህቶች ቢያነጋግሩን ደስ ይለናል። በዚህ መንገድ መጽሔቱ ለሚጠናበት ጊዜ ይደርስላቸዋል።
◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ጽሑፎች፦ በእንግሊዝኛ፦ የ1996 የዓመት መጽሐፍ፤ በጣልያንኛ፦ የ1996 የዓመት መጽሐፍ፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፤ በሲዳምኛ፦ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! እና ትራክት ቁጥር 15
◼ እንደገና የመጡልን፦ በእንግሊዝኛ፦ መለኮታዊ ስም፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ ጠቃሚ ነው፣ ለዘላለም መኖር (ትንሹ)፣ የሰው ልጅ ያደረገው ፍለጋ፣ መጽሐፌ፣ ባለማጣቀሻው መጽሐፍ ቅዱስ (አዓት Rbi-8)፤ በፈረንሳይኛ፦ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ ለዘላለም መኖር (ትንሹ)።