መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“በብዙ አካባቢዎች የሚኖሩ ጎረቤታሞች እንደ ድሮው እንደማይቀራረቡ አስተውለዋል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ኢየሱስ ጥሩ ጎረቤት ለመሆን የሚረዳ አንድ ወሳኝ መመሪያ ሰጥቷል። [ማቴዎስ 7:12ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ጥሩ ጎረቤት መሆንና ሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ መርዳት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይነግረናል።”
ንቁ! መስከረም 8
“ብዙ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡት የዓመፅና የሽብር ድርጊቶች በጣም ያሳስቧቸዋል። መክብብ 8:9 ላይ በሚገኘው በዚህ አባባል እርስዎም ይስማሙ ይሆናል። [ጥቅሱን አንብብለትና መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የንቁ! እትም ከታሪክ ምን ልንማር እንደምንችልና የሰው አገዛዝ በቅርቡ እንደሚጠፋ ያብራራል።”
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 15
“በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ‘ቅዱሳን’ ልዩ ኃይል እንዳላቸውና በእነርሱ አማላጅነት መጸለይ ጥሩ እንደሆነ ያምናሉ። እርስዎ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አመለካከት አለዎት? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህን በሚመለከት ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ብሎ እንደተናገረ ልብ ይበሉ። [ዮሐንስ 14:6ን አንብብ።] አንዳንዶች ይህን ጥቅስ ሲመለከቱ ‘በቅዱሳን’ በኩል መጸለይ ተገቢ ስለመሆኑ ይጠራጠራሉ። ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ይሰጣል።”
Sept. 22
“በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት ባዮሎጂያዊ ጦር መሣሪያዎችና ሽብርተኝነት ያሳስቧቸዋል። ሰብዓዊ መንግሥታት ሽብርተኝነትን ከዚህ ዓለም ላይ ጨርሰው ማጥፋት የሚችሉ ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ወደፊት ምን ለማድረግ እንዳሰበ ይናገራል። [ሕዝቅኤል 34:28ን አንብብለት።] ይህ የንቁ! መጽሔት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የሚናገረው ሐሳብ አለው።”