ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥር፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ የካቲት፦ የቤተሰብ ደስታ ወይም የአምላክ ቃል፤ መጋቢት፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ ሚያዝያ፦ መጽሔቶች።
◼ ከየካቲት ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚያቀርቡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “እውነት በሕይወታችሁ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?” የሚል ጭብጥ ይኖረዋል።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ የ2011 የዕለት ጥቅስ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በኪንያሩዋንዳ፣ በኦሮምኛ፣ በስዋሂሊና በትግርኛ፤ አማርኛ፦ ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው? የሕይወት አመጣጥ—መልስ የሚያሻቸው አምስት ጥያቄዎች፤ ቻይንኛ፦ ሰላምና ደስታ የሚያስገኝ ጎዳና (ለቡድሂስቶች)፤ እንግሊዝኛ፦ ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው? የሕይወት አመጣጥ—መልስ የሚያሻቸው አምስት ጥያቄዎች፣ በኤርምያስ በኩል የተላለፈልን የአምላክ ቃል፣ ሰላምና ደስታ የሚያስገኝ ጎዳና (ለቡድሂስቶች)፣ የ2011 የቀን መቁጠሪያ፤ በሲዲ፦ ለይሖዋ ዘምሩ— በድምፅ የተቀነባበረ ዲስክ 2፤ በዲቪዲ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ያሳዩት በተግባር የተፈተነ እምነት ክፍል 1፦ ከጨለማ መውጣት (ዲስኩ ፈረንሳይኛንና ሌሎች ቋንቋዎችን ይዟል)፤ ፈረንሳይኛ፦ የ2011 የቀን መቁጠሪያ፤ ሲዳምኛ፦ ትራክት ቁ. 20፤ ትግርኛ፦ በኤርምያስ በኩል የተላለፈልን የአምላክ ቃል።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ መጽሐፌ፣ የዳንኤል ትንቢት፣ ታላቅ ሰው፣ የአምላክ ቃል፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ ትራክት ቁ. 13, 14, 20, 21፤ አረብኛ፦ አዲስ ዓለም ትርጉም፤ እንግሊዝኛ፦ አዲስ ዓለም ትርጉም (በኪስ የሚያዝ)፣ ክርኤተር፣ ማንካይንድስ ሰርች፣ የሕይወት ዓላማ፣ ለይሖዋ ዘምሩ፣ ለይሖዋ ዘምሩ (በትልልቅ ፊደላት)፤ ፈረንሳይኛ፦ አዲስ ዓለም ትርጉም፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ለይሖዋ ዘምሩ፤ ሲዳምኛ፦ ትራክት ቁ. 14፤ ትግርኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት።