የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በዚህ የአገልግሎት ዓመት በመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ውስጥ 9,523 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር በመመዝገቡ 1.3 በመቶ ጭማሪ ተገኝቷል። በእነዚህ ወራት መጽሔት በማበርከት ረገድ 18 በመቶ ጭማሪ ታይቷል። ብሮሹሮችን በማበርከት ረገድም ካለፈው የአገልግሎት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በእነዚህ ወራት 10 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቧል፤ ይህም ወንድሞችና እህቶች በግሩም ሁኔታ የተዘጋጁትን ብሮሹሮች በተሻለ መንገድ እየተጠቀሙ እንዳለ የሚያሳይ ነው። ይህ ደግሞ በርካታ ሰዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር በር እንደሚከፍት እሙን ነው።