የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ታኅሣሥ 29, 2014 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
ሰው ሲሞትብን ሐዘናችንን ከምንገልጽበት መንገድ ጋር በተያያዘ በዘዳግም 14:1 ላይ ያለውን የራስን ሰውነት መቦጨቅን የሚከለክለውን ትእዛዝ ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? [ኅዳር 3, w04 9/15 ገጽ 27 አን. 4]
የእስራኤል ነገሥታት የአምላክን ሕግ ለራሳቸው እንዲገለብጡና ‘በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እንዲያነቡት’ የተደረገበት ዓላማ ምንድን ነው? (ዘዳ. 17:18-20) [ኅዳር 3, w02 6/15 ገጽ 12 አን. 4]
“በሬና አህያ አንድ ላይ ጠምደህ አትረስ” የሚለው ትእዛዝ የተሰጠው ለምንድን ነው? አቻ ባልሆነ መንገድ ስለ መጠመድ የሚገልጸው ይህ ትእዛዝ ለክርስቲያኖች የሚሠራው እንዴት ነው? (ዘዳ. 22:10) [ኅዳር 10, w03 10/15 ገጽ 32]
“ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም እንኳ ቢሆን፣ የብድር መያዣ” አድርጎ መውሰድ የተከለከለው ለምንድን ነው? (ዘዳ. 24:6) [ኅዳር 17, w04 9/15 ገጽ 26 አን. 3]
እስራኤላውያን ታዛዥ መሆን ያለባቸው በምን ዓይነት መንፈስ ነበር? እኛስ ይሖዋን እንድናገለግል የሚያነሳሳን ምን መሆን ይኖርበታል? (ዘዳ. 28:47) [ኅዳር 24, w10 9/15 ገጽ 8 አን. 4]
በዘዳግም 30:19, 20 ላይ የሚገኙት ሕይወት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ሦስት መሠረታዊ ብቃቶች ምንድን ናቸው? [ኅዳር 24, w10 2/15 ገጽ 28 አን. 17]
ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ድረስ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በሙሉ ቃል በቃል በለሆሳስ ወይም ድምፃችንን ዝቅ አድርገን ማንበብ ይጠበቅብናል? አብራራ። (ኢያሱ 1:8 NW) [ታኅ. 8, w13 4/15 ገጽ 7 አን. 4]
በኢያሱ 5:14, 15 ላይ የተጠቀሰው “የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ” ማን ነው? ይህ ዘገባ እኛን የሚያበረታታንስ እንዴት ነው? [ታኅ. 8, w04 12/1 ገጽ 9 አን. 1]
አካን ኃጢአት እንዲሠራ ያደረገው ምንድን ነው? እኛስ አካን ከተወው መጥፎ ምሳሌ ምን እንማራለን? (ኢያሱ 7:20, 21) [ታኅ. 15, w10 4/15 ገጽ 20-21 አን. 2, 5]
ካሌብ የተወው ምሳሌ የሚያበረታታን እንዴት ነው? (ኢያሱ 14:10-13) [ታኅ. 29, w04 12/1 ገጽ 12 አን. 2]