ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ይሖዋ ሆይ . . . በአንተ እታመናለሁ”
በጥሩም ሆነ በአስቸጋሪ ጊዜ በይሖዋ መታመናችን አስፈላጊ ነው። (መዝ 25:1, 2) በስምንተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. በይሁዳ የነበሩ የአምላክ ሕዝቦች በይሖዋ ላይ ያላቸውን እምነት የሚፈታተን ሁኔታ አጋጥሟቸው ነበር። በወቅቱ ከተፈጠሩት ሁኔታዎች ብዙ ትምህርት ማግኘት እንችላለን። (ሮም 15:4) “ይሖዋ ሆይ . . . በአንተ እታመናለሁ” የሚለውን ቪዲዮ ከተመለከትክ በኋላ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሞክር።
ሕዝቅያስ ምን አደጋ ተደቅኖበት ነበር?
ሕዝቅያስ ጠላት ሊወረው እንደሆነ ባወቀ ጊዜ በምሳሌ 22:3 ላይ የሚገኘውን መሠረታዊ ሥርዓት ተግባራዊ ያደረገው እንዴት ነው?
ሕዝቅያስ ለአሦራውያን እጁን መስጠት ወይም ከግብፅ ጋር ግንባር መፍጠር ያልፈለገው ለምንድን ነው?
ሕዝቅያስ ለክርስቲያኖች ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው?
በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት የሚፈትኑ ምን ሁኔታዎች ያጋጥሙናል?