ከመጋቢት 26–ሚያዝያ 1
ማቴዎስ 25
መዝሙር 143 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ”፦ (10 ደቂቃ)
ማቴ 25:1-6—አምስት ልባምና አምስት ሞኝ ደናግል ሙሽራውን ሊቀበሉ ወጥተው ነበር
ማቴ 25:7-10—ሙሽራው በደረሰበት ጊዜ ሞኞቹ ደናግል በቦታው አልነበሩም
ማቴ 25:11, 12—ወደ ሠርጉ ድግስ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ልባሞቹ ደናግል ብቻ ናቸው
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ማቴ 25:31-33—ስለ በጎቹና ስለ ፍየሎቹ የሚናገረውን ምሳሌ አብራራ። (w15 3/15 27 አን. 7)
ማቴ 25:40—የክርስቶስ ወንድሞች ወዳጅ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (w09 10/15 16 አን. 16-18)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ማቴ 25:1-23
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ግለሰቡ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኝ ጋብዝ።
ሦስተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመረጥከውን ጥቅስ ተጠቀም፤ ከዚያም አንድ የማስጠኛ ጽሑፍ አበርክት።
ንግግር፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) w15 3/15 27 አን. 7-10—ጭብጥ፦ ስለ በጎቹና ስለ ፍየሎቹ የሚናገረው ምሳሌ የስብከቱን ሥራ አስፈላጊነት የሚያጎላው እንዴት ነው?
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥናቶቻችን እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ማሳየት”፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። በርዕሱ ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አንዲት አስፋፊ፣ ጥናቷን እንዴት መዘጋጀት እንደምትችል ስታሠለጥናት የሚያሳየውን ቪዲዮ አጫውትና ተወያዩበት። አድማጮች ጥናቶቻቸውን እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ለማሠልጠን የተጠቀሙበትን ውጤታማ የሆነ ዘዴ እንዲናገሩ ጋብዝ።
ለእንግዶቻችን ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉ፦ (5 ደቂቃ) በመጋቢት 2016 የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አድማጮች በ2017 የጌታ ራት ወቅት ያገኟቸውን አስደሳች ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። መጋቢት 31 በሚከበረው የመታሰቢያ በዓል ወቅት መኪና ከማቆም፣ ወደ ስብሰባው ቦታ ከመግባትም ሆነ ከመውጣት እና ከመሳሰሉት ነገሮች ጋር በተያያዘ ስለተደረጉት ዝግጅቶች አስፈላጊውን ማሳሰቢያ ስጥ።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 5
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 95 እና ጸሎት