ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት 1 ሰማያትና ምድር ተፈጠሩ (1, 2) ምድር የተሰናዳችባቸው ስድስት ቀናት (3-31) የመጀመሪያ ቀን፦ ብርሃን፤ ቀንና ሌሊት (3-5) ሁለተኛ ቀን፦ ጠፈር (6-8) ሦስተኛ ቀን፦ የብስና ተክሎች (9-13) አራተኛ ቀን፦ በሰማያት ላይ ያሉ ብርሃን ሰጪ አካላት (14-19) አምስተኛ ቀን፦ ዓሣዎችና ወፎች (20-23) ስድስተኛ ቀን፦ በምድር ላይ የሚኖሩ እንስሳትና ሰዎች (24-31) 2 በሰባተኛው ቀን አምላክ ከሥራው አረፈ (1-3) የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ አምላክ (4) የመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት በኤደን ገነት (5-25) ሰው ከአፈር ተሠራ (7) የተከለከለው የእውቀት ዛፍ (15-17) ሴት ከአዳም ተፈጠረች (18-25) 3 ሰው ኃጢአት ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ (1-13) የመጀመሪያው ውሸት (4, 5) ይሖዋ በዓመፀኞቹ ላይ ያስተላለፈው ፍርድ (14-24) ስለ ሴቲቱ ዘር የተነገረ ትንቢት (15) ከኤደን ገነት ተባረሩ (23, 24) 4 ቃየንና አቤል (1-16) የቃየን ዘሮች (17-24) ሴትና ልጁ ሄኖስ (25, 26) 5 ከአዳም እስከ ኖኅ (1-32) አዳም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ (4) ሄኖክ ከአምላክ ጋር ሄደ (21-24) 6 የአምላክ ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች አገቡ (1-3) ኔፍሊሞች ተወለዱ (4) ይሖዋ በሰው ልጆች ክፋት አዘነ (5-8) ኖኅ መርከብ እንዲሠራ ተልእኮ ተሰጠው (9-16) አምላክ የጥፋት ውኃ እንደሚመጣ ተናገረ (17-22) 7 ወደ መርከቡ ገቡ (1-10) ምድር አቀፍ የጥፋት ውኃ (11-24) 8 የጥፋት ውኃው ከምድር ላይ እየቀነሰ ሄደ (1-14) ኖኅ ርግብ ላከ (8-12) ከመርከቡ ወጡ (15-19) አምላክ ምድርን በተመለከተ የገባው ቃል (20-22) 9 ለመላው የሰው ዘር የተሰጠ መመሪያ (1-7) ስለ ደም የተሰጠ ሕግ (4-6) የቀስተ ደመና ቃል ኪዳን (8-17) ስለ ኖኅ ዘሮች የተነገሩ ትንቢቶች (18-29) 10 የብሔራት ስም ዝርዝር (1-32) የያፌት ዘሮች (2-5) የካም ዘሮች (6-20) ናምሩድ ይሖዋን ተቃወመ (8-12) የሴም ዘሮች (21-31) 11 የባቤል ግንብ (1-4) ይሖዋ ቋንቋቸውን ዘበራረቀ (5-9) ከሴም እስከ አብራም (10-32) የታራ ቤተሰብ (27) አብራም ዑርን ለቆ ወጣ (31) 12 አብራም ከካራን ወደ ከነአን ሄደ (1-9) አምላክ ለአብራም የሰጠው ተስፋ (7) አብራምና ሦራ በግብፅ (10-20) 13 አብራም ወደ ከነአን ተመለሰ (1-4) አብራምና ሎጥ ተለያዩ (5-13) አምላክ ለአብራም በድጋሚ ተስፋ ሰጠው (14-18) 14 አብራም ሎጥን ታደገው (1-16) መልከጼዴቅ አብራምን ባረከው (17-24) 15 አምላክ ከአብራም ጋር የገባው ቃል ኪዳን (1-21) ለ400 ዓመት እንደሚጨቆኑ ትንቢት ተነገረ (13) አምላክ ለአብራም ዳግመኛ ቃል ገባለት (18-21) 16 አጋርና እስማኤል (1-16) 17 አብርሃም የብዙ ብሔራት አባት ይሆናል (1-8) አብራም፣ አብርሃም ተባለ (5) የግርዘት ቃል ኪዳን (9-14) ሦራ፣ ሣራ ተባለች (15-17) ይስሐቅ የሚባል ልጅ እንደሚወልድ ቃል ተገባለት (18-27) 18 ሦስት መላእክት ወደ አብርሃም መጡ (1-8) ሣራ ወንድ ልጅ እንደምትወልድ ቃል ተገባላት፤ እሷም ሳቀች (9-15) አብርሃም ስለ ሰዶም ያቀረበው ጥያቄ (16-33) 19 መላእክት ወደ ሎጥ መጡ (1-11) ሎጥና ቤተሰቡ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው (12-22) ሰዶምና ገሞራ ጠፉ (23-29) የሎጥ ሚስት የጨው ዓምድ ሆነች (26) ሎጥና ሴቶች ልጆቹ (30-38) የሞዓባውያንና የአሞናውያን መገኛ (37, 38) 20 አቢሜሌክ ሣራን ለአብርሃም መለሰለት (1-18) 21 ይስሐቅ ተወለደ (1-7) እስማኤል በይስሐቅ ላይ አፌዘበት (8, 9) አጋርና እስማኤል ተባረሩ (10-21) አብርሃም ከአቢሜሌክ ጋር የገባው ቃል ኪዳን (22-34) 22 አብርሃም ይስሐቅን መሥዋዕት እንዲያደርግ ተጠየቀ (1-19) በአብርሃም ዘር አማካኝነት የሚገኝ በረከት (15-18) የርብቃ ቤተሰብ (20-24) 23 ሣራ ሞታ ተቀበረች (1-20) 24 ለይስሐቅ ሚስት መፈለግ (1-58) ርብቃ ወደ ይስሐቅ ሄደች (59-67) 25 አብርሃም በድጋሚ አገባ (1-6) አብርሃም ሞተ (7-11) የእስማኤል ወንዶች ልጆች (12-18) ያዕቆብና ኤሳው ተወለዱ (19-26) ኤሳው የብኩርና መብቱን ሸጠ (27-34) 26 ይስሐቅና ርብቃ በጌራራ ኖሩ (1-11) አምላክ የሰጠውን ተስፋ በድጋሚ ለይስሐቅ አረጋገጠለት (3-5) በውኃ ጉድጓዶች የተነሳ የተፈጠረ ግጭት (12-25) ይስሐቅ ከአቢሜሌክ ጋር የገባው ቃል ኪዳን (26-33) ሁለቱ የኤሳው ሂታውያን ሚስቶች (34, 35) 27 ይስሐቅ ያዕቆብን ባረከው (1-29) ኤሳው መባረክ ቢፈልግም በድርጊቱ አልተጸጸተም (30-40) ኤሳው ያዕቆብን ጠላው (41-46) 28 ይስሐቅ ያዕቆብን ወደ ጳዳንአራም ላከው (1-9) ያዕቆብ በቤቴል ያለመው ሕልም (10-22) አምላክ የሰጠውን ተስፋ በድጋሚ ለያዕቆብ አረጋገጠለት (13-15) 29 ያዕቆብ ከራሔል ጋር ተገናኘ (1-14) ያዕቆብ ራሔልን ወደዳት (15-20) ያዕቆብ ሊያንና ራሔልን አገባ (21-29) ያዕቆብ ከሊያ የወለዳቸው አራት ወንዶች ልጆች፦ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊና ይሁዳ (30-35) 30 ባላ ዳንንና ንፍታሌምን ወለደች (1-8) ዚልጳ ጋድንና አሴርን ወለደች (9-13) ሊያ ይሳኮርንና ዛብሎንን ወለደች (14-21) ራሔል ዮሴፍን ወለደች (22-24) የያዕቆብ መንጋ እየበዛ ሄደ (25-43) 31 ያዕቆብ በድብቅ ወደ ከነአን ኮበለለ (1-18) ላባ ያዕቆብን ተከታትሎ ደረሰበት (19-35) ያዕቆብ ከላባ ጋር የገባው ቃል ኪዳን (36-55) 32 መላእክት ያዕቆብን አገኙት (1, 2) ያዕቆብ ከኤሳው ጋር ለመገናኘት ተዘጋጀ (3-23) ያዕቆብ ከአንድ መልአክ ጋር ታገለ (24-32) ያዕቆብ፣ እስራኤል ተባለ (28) 33 ያዕቆብ ከኤሳው ጋር ተገናኘ (1-16) ያዕቆብ ወደ ሴኬም ተጓዘ (17-20) 34 ዲና ተደፈረች (1-12) የያዕቆብ ወንዶች ልጆች የተንኮል ድርጊት ፈጸሙ (13-31) 35 ያዕቆብ ባዕዳን አማልክትን አስወገደ (1-4) ያዕቆብ ወደ ቤቴል ተመለሰ (5-15) ቢንያም ተወለደ፤ ራሔል ሞተች (16-20) የእስራኤል 12 ወንዶች ልጆች (21-26) ይስሐቅ ሞተ (27-29) 36 የኤሳው ዘሮች (1-30) የኤዶም ነገሥታትና አለቆች (31-43) 37 የዮሴፍ ሕልሞች (1-11) ዮሴፍና ቅናት ያደረባቸው ወንድሞቹ (12-24) ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ (25-36) 38 ይሁዳና ትዕማር (1-30) 39 ዮሴፍ በጶጢፋር ቤት (1-6) ዮሴፍ ከጶጢፋር ሚስት ሸሸ (7-20) ዮሴፍ እስር ቤት ተጣለ (21-23) 40 ዮሴፍ የእስረኞቹን ሕልም ፈታላቸው (1-19) “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?” (8) የፈርዖን የልደት በዓል (20-23) 41 ዮሴፍ የፈርዖንን ሕልሞች ፈታለት (1-36) ፈርዖን ዮሴፍን ከፍ ከፍ አደረገው (37-46ሀ) ዮሴፍ እህል እንዲያከፋፍል ተሾመ (46ለ-57) 42 የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ግብፅ ሄዱ (1-4) ዮሴፍ ከወንድሞቹ ጋር ተገናኘ፤ እንዲሁም ፈተናቸው (5-25) የዮሴፍ ወንድሞች ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ተመለሱ (26-38) 43 የዮሴፍ ወንድሞች ቢንያምን ይዘው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ግብፅ ሄዱ (1-14) ዮሴፍ በድጋሚ ከወንድሞቹ ጋር ተገናኘ (15-23) ዮሴፍ ከወንድሞቹ ጋር በማዕድ ተቀመጠ (24-34) 44 የዮሴፍ የብር ጽዋ በቢንያም ከረጢት ውስጥ ተገኘ (1-17) ይሁዳ ስለ ቢንያም ተማጸነ (18-34) 45 ዮሴፍ ለወንድሞቹ ማንነቱን ገለጠላቸው (1-15) የዮሴፍ ወንድሞች ያዕቆብን ይዘው ለመምጣት ሄዱ (16-28) 46 ያዕቆብና ቤተሰቡ ወደ ግብፅ ሄዱ (1-7) ወደ ግብፅ የሄዱት ሰዎች ስም ዝርዝር (8-27) ዮሴፍ በጎሸን ከያዕቆብ ጋር ተገናኘ (28-34) 47 ያዕቆብ ከፈርዖን ጋር ተገናኘ (1-12) የዮሴፍ ጥበብ የተሞላበት አስተዳደር (13-26) እስራኤል በጎሸን መኖር ጀመረ (27-31) 48 ያዕቆብ የዮሴፍን ሁለት ወንዶች ልጆች ባረካቸው (1-12) ኤፍሬም የበለጠ በረከት አገኘ (13-22) 49 ያዕቆብ ሊሞት በተቃረበበት ጊዜ የተናገረው ትንቢት (1-28) ሴሎ ከይሁዳ ይወጣል (10) ያዕቆብ ስለሚቀበርበት ሁኔታ የሰጠው ትእዛዝ (29-32) ያዕቆብ ሞተ (33) 50 ዮሴፍ ያዕቆብን በከነአን ቀበረው (1-14) ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር እንዳላቸው በድጋሚ አረጋገጠላቸው (15-21) ዮሴፍ የሚሞትበት ጊዜ ቀረበ (22-26) ዮሴፍ አፅሙን አስመልክቶ የሰጠው ትእዛዝ (25)