ዘኁልቁ የመጽሐፉ ይዘት 1 በሠራዊቱ ውስጥ እንዲያገለግሉ የተመዘገቡት ወንዶች (1-46) ሌዋውያን ከወታደራዊ አገልግሎት ነፃ ናቸው (47-51) እስራኤላውያን በየምድባቸው በሥርዓት ይሰፍራሉ (52-54) 2 ሦስት ነገዶችን ባቀፈ ምድብ ተከፋፍለው ይሰፍራሉ (1-34) የይሁዳ ምድብ በስተ ምሥራቅ ይሰፍራል (3-9) የሮቤል ምድብ በስተ ደቡብ ይሰፍራል (10-16) ሌዊ መሃል ላይ ይሰፍራል (17) የኤፍሬም ምድብ በስተ ምዕራብ ይሰፍራል (18-24) የዳን ምድብ በስተ ሰሜን ይሰፍራል (25-31) የተመዘገቡት ወንዶች ጠቅላላ ቁጥር (32-34) 3 የአሮን ወንዶች ልጆች (1-4) ሌዋውያን እንዲያገለግሉ ተመረጡ (5-39) በኩሮቹን መዋጀት (40-51) 4 ቀአታውያን የሚያከናውኑት አገልግሎት (1-20) ጌድሶናውያን የሚያከናውኑት አገልግሎት (21-28) ሜራራውያን የሚያከናውኑት አገልግሎት (29-33) የቆጠራው ውጤት (34-49) 5 የረከሱ ሰዎች ተገልለው እንዲቆዩ ማድረግ (1-4) ኃጢአትን መናዘዝና ካሳ መክፈል (5-10) በዝሙት የተጠረጠረችን ሚስት እርግማን በሚያመጣው ውኃ መፈተን (11-31) 6 የናዝራዊነት ስእለት (1-21) ካህናት የሚባርኩበት መንገድ (22-27) 7 የማደሪያ ድንኳኑ ሲመረቅ የቀረቡ መባዎች (1-89) 8 አሮን ሰባቱን መብራቶች ለኮሰ (1-4) ሌዋውያኑ ነጽተው ማገልገል ጀመሩ (5-22) ሌዋውያን የሚያገለግሉበት የዕድሜ ገደብ (23-26) 9 የፋሲካን በዓል በቀኑ ማክበር ላልቻለ ሰው የተደረገ ዝግጅት (1-14) በማደሪያ ድንኳኑ ላይ የታየው ደመናና እሳት (15-23) 10 ከብር የተሠሩት መለከቶች (1-10) ከሲና ተነስተው ጉዞ ጀመሩ (11-13) የጉዞ ቅደም ተከተላቸው (14-28) ሆባብ እስራኤላውያንን መንገድ እንዲያሳይ ተጠየቀ (29-34) ሙሴ፣ እስራኤላውያን ድንኳናቸውን ነቀለው ሲነሱ ያቀረበው ጸሎት (35, 36) 11 ከይሖዋ የመጣ እሳት ባጉረመረሙት ሰዎች ላይ ነደደ (1-3) የምንበላው ሥጋ አጣን ብለው አለቀሱ (4-9) ሙሴ የእስራኤል ሕዝብ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ ተሰማው (10-15) ይሖዋ መንፈሱን ለ70ዎቹ ሽማግሌዎች ሰጠ (16-25) ኤልዳድና ሞዳድ፤ ኢያሱ ለሙሴ ተቆረቆረ (26-30) ድርጭቶች በሰፈሩ ዙሪያ ተበተኑ፤ ሕዝቡ በመስገብገቡ ተቀጣ (31-35) 12 ሚርያምና አሮን ሙሴን ነቀፉት (1-3) ሙሴ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገር ነበር (3) ይሖዋ ለሙሴ ተሟገተለት (4-8) ሚርያም በሥጋ ደዌ ተመታች (9-16) 13 አሥራ ሁለቱ ሰላዮች ወደ ከነአን ተላኩ (1-24) አሥሩ ሰላዮች ያመጡት መጥፎ ወሬ (25-33) 14 ሕዝቡ ወደ ግብፅ መመለስ ፈለገ (1-10) ኢያሱና ካሌብ ያመጡት መልካም ወሬ (6-9) ይሖዋ ተቆጣ፤ ሙሴ ስለ ሕዝቡ ማለደ (11-19) በምድረ በዳ 40 ዓመት እንዲንከራተቱ ተፈረደባቸው (20-38) እስራኤላውያን በአማሌቃውያን ድል ተመቱ (39-45) 15 መባን አስመልክቶ የተሰጠ ሕግ (1-21) ለእስራኤላውያንም ሆነ አብረዋቸው ለሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች አንድ ዓይነት ሕግ ተሰጠ (15, 16) ባለማወቅ ለተፈጸመ ኃጢአት የሚቀርብ መባ (22-29) ሆን ብሎ ኃጢአት መሥራት የሚያስከትለው ቅጣት (30, 31) የሰንበትን ሕግ የጣሰው በሞት ተቀጣ (32-36) እስራኤላውያን በልብሳቸው ጫፍ ላይ ዘርፍ እንዲያደርጉ ተነገራቸው (37-41) 16 ቆሬ፣ ዳታንና አቤሮን ዓመፁ (1-19) ዓመፀኞቹ ተቀጡ (20-50) 17 የአሮን በትር አበበች (1-13) 18 የካህናቱና የሌዋውያኑ የሥራ ድርሻ (1-7) የካህናቱ ድርሻ (8-19) የጨው ቃል ኪዳን (19) ሌዋውያን አሥራት መቀበልና ካገኙት ላይ አሥራት መስጠት ይጠበቅባቸዋል (20-32) 19 ቀይ ላምና የሚያነጻው ውኃ (1-22) 20 ሚርያም በቃዴስ ሞታ ተቀበረች (1) ሙሴ ከዓለቱ ውኃ አፈለቀ፤ እንዲሁም ኃጢአት ሠራ (2-13) ኤዶማውያን፣ እስራኤላውያን ክልላቸውን አቋርጠው እንዳያልፉ ከለከሉ (14-21) አሮን ሞተ (22-29) 21 የአራድ ንጉሥ ድል ተመታ (1-3) የመዳብ እባብ (4-9) እስራኤላውያን በሞዓብ ክልል ዞረው ሄዱ (10-20) አሞራዊው ንጉሥ ሲሖን ድል ተመታ (21-30) አሞራዊው ንጉሥ ኦግ ድል ተመታ (31-35) 22 ባላቅ፣ እስራኤላውያንን እንዲረግምለት በለዓምን ቀጠረ (1-21) የበለዓም አህያ ተናገረች (22-41) 23 የመጀመሪያው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (1-12) ሁለተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (13-30) 24 ሦስተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (1-11) አራተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (12-25) 25 እስራኤላውያን ከሞዓብ ሴቶች ጋር የፆታ ብልግና ፈጸሙ (1-5) ፊንሃስ እርምጃ ወሰደ (6-18) 26 ሁለተኛው የእስራኤላውያን የሕዝብ ቆጠራ (1-65) 27 የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች (1-11) ኢያሱ ሙሴን እንደሚተካ ተነገረው (12-23) 28 የተለያዩ መባዎች የሚቀርቡበት መንገድ (1-31) ዘወትር የሚቀርብ መባ (1-8) በየሰንበቱ የሚቀርብ መባ (9, 10) በየወሩ የሚቀርብ መባ (11-15) በፋሲካ በዓል የሚቀርብ መባ (16-25) በሳምንታት በዓል የሚቀርብ መባ (26-31) 29 የተለያዩ መባዎች የሚቀርቡበት መንገድ (1-40) መለከት የሚነፋበት ቀን (1-6) የስርየት ቀን (7-11) የዳስ በዓል (12-38) 30 አንድ ወንድ ስእለት ቢሳል (1, 2) አንዲት ወጣት ወይም አንዲት ሴት ስእለት ብትሳል (3-16) 31 በምድያም ላይ የተወሰደ የበቀል እርምጃ (1-12) በለዓም ተገደለ (8) የጦር ምርኮን በተመለከተ የተሰጠ መመሪያ (13-54) 32 ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያሉ የሰፈራ መንደሮች (1-42) 33 እስራኤላውያን በምድረ በዳ ያደረጉት ጉዞ (1-49) ከነአናውያንን ድል አድርጎ ስለማባረር የተሰጠ መመሪያ (50-56) 34 የከነአን ወሰኖች (1-15) ምድሪቱን እንዲያከፋፍሉ የተመደቡት ወንዶች (16-29) 35 ለሌዋውያን የተሰጡ ከተሞች (1-8) የመማጸኛ ከተሞች (9-34) 36 ውርስ የሚሰጣቸው ሴቶች የሚያገቡትን ሰው በተመለከተ የወጣ ሕግ (1-13)