ቤተሰብ የሚወያይበት
ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
ዳንኤል 6:1-24ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ፤ እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን የጎደሉትን ነገሮች ቦታ ቦታቸው ላይ ሳልና ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።
1. ․․․․․
2. ․․․․․
ለውይይት፦
ዳንኤል እዚህ ቦታ የተጣለው ለምንድን ነው? ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግህ ምክንያት ችግር ደርሶብህ ያውቃል? እስቲ ምን እንዳጋጠመህ ግለጽ። ችግር የሚያስከትል ቢሆን እንኳ ትክክል የሆነውን ማድረግ ምን ጥቅም ያስገኛል?
ፍንጭ፦ 1 ጴጥሮስ 2:19-21ን አንብብ።
ስለ ሐዋርያው ማቴዎስ ምን የምታውቀው ነገር አለ?
3. የማቴዎስ ሌላኛው ስሙ ማን ነው?
ፍንጭ፦ ማቴዎስ 9:9ን እና ማርቆስ 2:14ን አንብብ።
․․․․․
4. ማቴዎስ የኢየሱስ ተከታይ ለመሆን ሲል ምን መሥዕዋት ከፍሏል?
ፍንጭ፦ ሉቃስ 5:27, 28ን አንብብ።
․․․․․
ለውይይት፦
የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መሆን የምትፈልግ ከሆነ ምን መሥዋዕትነት መክፈል ሊያስፈልግህ ይችላል? የምታገኛቸው አንዳንድ በረከቶችስ ምንድን ናቸው?
ፍንጭ፦ ማርቆስ 10:28-30ን አንብብ።
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
ከዚህ እትም
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።
ገጽ 6 ሁሉን ነገር የሠራው ማን ነው? ዕብራውያን 3:․․․
ገጽ 7 ክፉዎች ምን ይደርስባቸዋል? ምሳሌ 2:․․․
ገጽ 20 ወደ አብ መቅረብ የሚቻለው በማን በኩል ብቻ ነው? ዮሐንስ 14:․․․
ገጽ 21 ለእነማን መጸለይ አለብን? ያዕቆብ 5:․․․
● መልሶቹ በገጽ 12 ላይ ይገኛሉ
በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. አንበሶቹ።
2. መልአኩ።
3. ሌዊ።
4. ሁሉንም ነገር ትቷል።