ትምህርት 15
ሌሎች የአምላክን ፈቃድ እንዲያደርጉ መርዳት
ስለ ተማርካቸው ነገሮች ለሌሎች መናገር የሚኖርብህ ለምንድን ነው? (1)
ምሥራቹን ለእነማን ማካፈል ትችላለህ? (2)
ጠባይህ በሌሎች ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል? (2)
ከጉባኤው ጋር በስብከቱ ሥራ ልትካፈል የምትችለው መቼ ነው? (3)
1. እስከ አሁን ብዙ ጥሩ ነገሮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ሳትማር አልቀረህም። ይህ ያገኘኸው እውቀት ክርስቲያናዊ ባሕርያትን እንድትኮተኩት ሊያደርግህ ይገባል። (ኤፌሶን 4:22-24) እንዲህ ያለው እውቀት የዘላለም ሕይወት ለማግኘት የግድ አስፈላጊ ነው። (ዮሐንስ 17:3) ይሁን እንጂ ሌሎች ሰዎችም ሕይወት እንዲያገኙ ምሥራቹን መስማት ያስፈልጋቸዋል። እውነተኛ ክርስቲያኖች በሙሉ ለሌሎች ሰዎች መመስከር ይኖርባቸዋል። ይህ የአምላክ ትእዛዝ ነው።—ሮሜ 10:10፤ 1 ቆሮንቶስ 9:16፤ 1 ጢሞቴዎስ 4:16
2. የምትማራቸውን መልካም ነገሮች በአካባቢህ ለሚገኙ ሰዎች በመናገር ምሥክርነት መስጠት ትችላለህ። ለቤተሰቦችህ፣ ለወዳጆችህ፣ ለትምህርት ቤትና ለመሥሪያ ቤት ባልደረቦችህ ተናገር። ይህን በምታደርግበት ጊዜ ደግና ታጋሽ ሁን። (2 ጢሞቴዎስ 2:24, 25) ሰዎች አንድ ሰው ከሚናገረው ነገር ይበልጥ የሚያደርጋቸውን ነገሮችና ጠባዩን እንደሚመለከቱ አስታውስ። ስለዚህ የምታሳየው ጥሩ ጠባይ ሌሎች ሰዎች የምትናገረውን መልእክት እንዲያዳምጡ ሊያደርጋቸው ይችላል።—ማቴዎስ 5:16፤ 1 ጴጥሮስ 3:1, 2, 16
3. ከጊዜ በኋላ በአካባቢህ ካለው የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ ጋር ተሰማርተህ ለመስበክ ብቁ ትሆናለህ። ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነ እርምጃ ነው። (ማቴዎስ 24:14) አንድ ሰው የይሖዋ አገልጋይ ሆኖ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኝ መርዳት መቻል እንዴት ያለ ታላቅ ደስታ ነው!—1 ተሰሎንቄ 2:19, 20