መዝሙር 28
አዲሱ መዝሙር
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 98)
1. ዘምሩ ላምላክ፤ አዲስ የውዳሴ መዝሙር።
አውሩ፣ ተናገሩ የሱን ታላቅ ተግባር።
ድል አድራጊ ነው፤ ኃያል ክንዱን አሳይቷል።
ፍትሕን ይወዳል፤ በጽድቅም ይፈርዳል።
(አዝማች)
ዘምሩ! አዲሱን ዝማሬ!
ዘምሩ! ያህ ንጉሥ ነው ሁሌ!
2. ለንጉሣችን እንዘምርለት በደስታ!
ስሙን አወድሱ፤ ከፍ አ’ርጉት በልልታ።
ሕዝቦቹ ሁሉ ላምላክ በኅብረት ዘምሩ።
መለከት፣ በገናም ያህን ያመስግኑ።
(አዝማች)
ዘምሩ! አዲሱን ዝማሬ!
ዘምሩ! ያህ ንጉሥ ነው ሁሌ!
3. ባሕሮችና በውስጣቸው ያለው ሕይወት፣
የምድርም ፍጥረታት እሱን ያወድሱት።
ምድሩም ሐሴትያ’ርግ፤ ወንዞች ሁሉ ያጨብጭቡ።
ተራሮች፣ ኮረብቶች ክብሩን ያስተጋቡ።
(አዝማች)
ዘምሩ! አዲሱን ዝማሬ!
ዘምሩ! ያህ ንጉሥ ነው ሁሌ!