መዝሙር 80
“ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም”
በወረቀት የሚታተመው
1. ያገልግሎት መብት ልዩ ነው፤
ከፍ አድርገን የምናየው።
ለአምላክ ሥራ ቅድሚያ በመስጠት
ቃሉን እንስበክ በትጋት።
(አዝማች)
‘ቀምሳችሁ እዩ ጥሩነቱን’
ብሎ ጋብዞናል ቃሉ።
ይባርከናል አምላካችን፤
ሰጥተናል ምርጣችንን።
2. የሙሉ ጊዜ አገልጋይ
ብዙ በረከት ያገኛል።
ባምላክ ላይ እምነት ስለሚኖረው፣
አይሰጋም፤ ባለው ይረካል።
(አዝማች)
‘ቀምሳችሁ እዩ ጥሩነቱን’
ብሎ ጋብዞናል ቃሉ።
ይባርከናል አምላካችን፤
ሰጥተናል ምርጣችንን።
(በተጨማሪም ማር. 14:8ን፣ ሉቃስ 21:2ን፣ 1 ጢሞ. 1:12ን እና 6:6ን ተመልከት።)