የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል በአገልግሎታችሁ ተጠቀሙበት
አንድ ሰው ምሥራቹን ለመስማት ፈቃደኛ በሚሆንበት ጊዜ አጋጣሚውን በተሻለ መንገድ መጠቀም ይኖርብናል፤ በዚህ ጊዜ ጥቅሶችን በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በማንበብ የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል እንደምንጠቀምበት ማሳየት እንችላለን። ይህ ሐሳብ ባለፈው ዓመት ባደረግነው ልዩ ስብሰባ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ “የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል በአገልግሎታችሁ ተጠቀሙበት” የሚል ንግግር አቅርቦ ነበር። ታዲያ ዋና ዋና ነጥቦቹን ታስታውሷቸዋላችሁ?
እኛ ከምንናገረው ይልቅ የይሖዋ ቃል ይበልጥ ኃይል ያለው ለምንድን ነው?—2 ጢሞ. 3:16, 17
መጽሐፍ ቅዱስ ስሜታችንን የሚያነሳሳው፣ አስተሳሰባችንን የሚቀርጸው፣ ዝንባሌያችንን የሚያጠራውና ባሕርያችንን የሚያስተካክለው እንዴት ነው?—የሰኔ 15, 2012 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 27 አን. 7ን ተመልከት።
በአገልግሎት ላይ ላገኘነው ሰው ጥቅስ ስናነብ ለአምላክ ቃል ትልቅ ቦታ እንዲሰጥ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?—የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 148 ከአን. 3-4ን እና የመጋቢት 2013 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 አን. 8ን ተመልከት።
ያነበብነውን ጥቅስ ማብራራትና ከተነሳው ነጥብ ጋር እንዲያገናዝቡ መርዳት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የሚቻለውስ እንዴት ነው?—ሥራ 17:2, 3፤ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 154 ከአን. 4 እስከ ገጽ 156 አን. 4 ተመልከት።