ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሉቃስ 8-9
የኢየሱስ ተከታይ ለመሆን ምን ያስፈልጋል?
አንድ ገበሬ ቀጥ ያለ ትልም ማውጣት ከፈለገ ከኋላው ያለው ነገር ትኩረቱን እንዲከፋፍለው መፍቀድ የለበትም። በተመሳሳይም አንድ ክርስቲያን፣ ዓለም ውስጥ ትቷቸው የመጣቸው ነገሮች ትኩረቱን እንዲከፋፍሉት መፍቀድ የለበትም።—ፊልጵ 3:13
አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ቀደም ሲል ምናልባትም እውነትን ከመስማታችን በፊት የነበረን ሕይወት የተሻለ እንደሆነ በማሰብ ያን ጊዜ መናፈቅ ልንጀምር እንችላለን። አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ እንዲህ ስናደርግ በዚያን ወቅት የነበረንን ደስታ አጋነን፣ ችግሮቻችንን ግን አቃለን ልንመለከት እንችላለን። እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ እንዲህ ተሰምቷቸው ነበር። (ዘኁ 11:5, 6) እኛም እንዲህ ባሉ ሐሳቦች ላይ የምናውጠነጥን ከሆነ ወደ ቀድሞው ሕይወታችን ለመመለስ ልንፈተን እንችላለን። እንግዲያው አሁን ባሉን በረከቶች ላይ ማሰላሰላችንና ወደፊት በአምላክ መንግሥት ሥር በምናገኘው ደስታ ላይ ማተኮራችን ምንኛ የተሻለ ነው!—2ቆሮ 4:16-18