ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 25–26
የማደሪያ ድንኳኑ ዋነኛ ዕቃ
በማደሪያ ድንኳኑም ሆነ በእስራኤል ሰፈር የነበረው ከሁሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ ዕቃ ታቦቱ ነበር። የአምላክን መገኘት የሚያመለክተው ደመና ከታቦቱ የስርየት መክደኛ በላይ ባሉት ሁለት ኪሩቦች መሃል ይታይ ነበር። በዓመታዊው የስርየት ቀን ሊቀ ካህናቱ የእስራኤላውያንን ኃጢአት ለማስተሰረይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ በመግባት የወይፈኑንና የፍየሉን ደም በመክደኛው ፊት ይረጨዋል። (ዘሌ 16:14, 15) ይህም ታላቁ ሊቀ ካህናት የሆነው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ገብቶ በአምላክ ፊት የቤዛዊ መሥዋዕቱን ዋጋ እንደሚያቀርብ የሚያሳይ ጥላ ሆኖ አገልግሏል።—ዕብ 9:24-26
የሚከተሉትን ጥቅሶች ቤዛው ከሚያስገኝልን በረከቶች ጋር አዛምድ፦
በረከት
ለዘላለም የመኖር ተስፋ
የኃጢአት ይቅርታ
ንጹሕ ሕሊና
እነዚህን በረከቶች ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብናል?