መዝሙር አንደኛ መጽሐፍ (መዝሙር 1-41) 1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣በኃጢአተኞች መንገድ+ የማይቆም፣በፌዘኞችም+ ወንበር የማይቀመጥ ሰው ደስተኛ ነው። 2 ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤+ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል።*+ 3 በጅረቶች ዳር እንደተተከለ፣ፍሬውን በወቅቱ እንደሚሰጥ፣ቅጠሉም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል። የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።+ 4 ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፤ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው። 5 ከዚህም የተነሳ ክፉዎች በፍርድ ፊት ለዘለቄታው አይቆሙም፤+ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ ጸንተው አይቆሙም።+ 6 ይሖዋ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፤+የክፉዎች መንገድ ግን ይጠፋል።+