-
ክፋት እስከ ዛሬ ያልተወገደው ለምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—2007 | መስከረም 15
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ በወቅቱ ምን እንደተፈጠረ ይነግረናል? ሰይጣን ዲያብሎስ በአንድ እባብ በመጠቀም ሔዋንን “በእርግጥ እግዚአብሔር፣ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉ’ ብሎአልን?” ሲል ጠየቃት። ሔዋን፣ አምላክ የሰጣቸውን ትእዛዝ በነገረችው ጊዜ ሰይጣን እንዲህ አላት:- “መሞት እንኳ አትሞቱም፤ ከፍሬው በበላችሁ ጊዜ ዐይናችሁ እንደሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ፣ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው።” ከዚያም ሔዋን የዛፉ ፍሬ የሚጓጓ ሆኖ ስለታያት “ከፍሬው ወስዳ በላች።” አክሎም ዘገባው “ከእርሷም ጋር ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ” ይላል። (ዘፍጥረት 3:1-6) በመሆኑም አዳምና ሔዋን የተሰጣቸውን የመምረጥ ነፃነት በአግባቡ ሳይጠቀሙበት ቀሩ እንዲሁም አምላክን ባለመታዘዝ ኃጢአት ሠሩ።
የተፈጸመው ሁኔታ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ተገንዝበሃል? ዲያብሎስ የተናገረው ነገር አምላክ ለአዳም ከሰጠው ትእዛዝ ጋር ይቃረናል። ሰይጣን አዳምና ሔዋን ክፉና መልካሙን ለመወሰን የይሖዋ እርዳታ እንደማያስፈልጋቸው በተዘዋዋሪ መንገድ ተናግሯል። በመሆኑም የሰይጣን ግድድር ይሖዋ ባለው የሰው ልጆችን የመግዛት ሕጋዊ መብት ላይ ጥያቄ አስነስቷል። በዚህም የተነሳ ሰይጣን ያስነሳው እጅግ ወሳኝ ጥያቄ ‘ይሖዋ የሰው ልጆችን የመግዛት መብት አለው?’ የሚለው ነው። ታዲያ እውነተኛው አምላክ ለዚህ ግድድር ምን ምላሽ ይሰጥ ይሆን?
-
-
ክፋት እስከ ዛሬ ያልተወገደው ለምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—2007 | መስከረም 15
-
-
ከዚህም በተጨማሪ ሰይጣን፣ ለሔዋን እንዲህ ብሏታል:- “ከፍሬው [እንዳይበሉ ከተከለከሉት ፍሬ] በበላችሁ ጊዜ ዐይናችሁ እንደሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ፣ እንደ እግዚአብሔር እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው።” (ዘፍጥረት 3:5) ሰይጣን እንዲህ ያለ አሳሳች ሐሳብ በማቅረብ የሰው ልጆች ራሳቸውን የመምራት አጋጣሚ እንዳላቸው ገለጸ። በዚህ መንገድ ሰዎች ከአምላክ ርቀው ራሳቸውን ቢመሩ የተሻለ ሕይወት እንደሚኖራቸው በመጠቆም የመጀመሪያዎቹን ባልና ሚስት አሳታቸው። ይሁን እንጂ ሰይጣን ያቀረበው ሐሳብ እውነት ነው?
በታሪክ ዘመናት ሁሉ የተለያዩ መንግሥታት ተፈራርቀዋል። የሰው ልጆች አሉ የተባሉትን ሁሉንም ዓይነት አገዛዞች ሞክረዋል። ይሁንና በሰው ልጆች ላይ አሰቃቂ ነገሮች በተደጋጋሚ ጊዜያት ደርሰዋል። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ከዛሬ 3,000 ዓመታት ገደማ በፊት ‘ሰው ሰውን የሚገዛው ለመጕዳት ነው’ ወደሚል ምክንያታዊ መደምደሚያ ደርሷል። (መክብብ 8:9) ነቢዩ ኤርምያስ ‘ሰው አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ አይችልም’ ሲል ጽፏል። (ኤርምያስ 10:23) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስክ የተገኙት ስኬቶች የዚህን አባባል እውነተኝነት ውድቅ ማድረግ አልቻሉም። ያለፉት ጊዜያት ከላይ የተጠቀሱት ሁለት አስተያየቶች እውነት መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
-