-
ይህ ዓለም ወደ ፍጻሜው የሚመጣው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2012 | መስከረም 15
-
-
15. ከአርማጌዶን በኋላ ሰይጣንና አጋንንቱ ምን ይሆናሉ?
15 በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሰይጣን ዓይኑ እያየ በምድር ላይ ያለው ድርጅቱ በሙሉ ሙልጭ ብሎ ይጠፋል። ከዚያም ተረኛው ራሱ ሰይጣን ይሆናል። ቀጥሎ የሚከናወነውን ነገር ሐዋርያው ዮሐንስ ገልጾታል። (ራእይ 20:1-3ን አንብብ።) “የጥልቁን ቁልፍ” የያዘው መልአክ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ ሰይጣንንና አጋንንቱን ይዞ ወደ ጥልቁ ይወረውራቸዋል፤ በዚያም ለአንድ ሺህ ዓመት ይቆያሉ። (ሉቃስ 8:30, 31፤ 1 ዮሐ. 3:8) ይህ ክንውን የእባቡ ራስ የሚቀጠቀጥበት የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው።c—ዘፍ. 3:15
-
-
ይህ ዓለም ወደ ፍጻሜው የሚመጣው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2012 | መስከረም 15
-
-
c የእባቡ ራስ የሚቀጠቀጥበት የመጨረሻው ምዕራፍ የሚፈጸመው በሺህ ዓመቱ ማብቂያ ላይ ሰይጣንና አጋንንቱ “ወደ እሳቱና ወደ ድኙ ሐይቅ” ሲወረወሩ ነው።—ራእይ 20:7-10፤ ማቴ. 25:41
-