-
መጽናናትን ለማግኘት ይሖዋን ተስፋ አድርግመጠበቂያ ግንብ—1996 | ኅዳር 1
-
-
6. (ሀ) የሰው ልጅ ኃጢአት ከሠራ በኋላ አምላክ ምን የሚያጽናና ተስፋ ሰጠ? (ለ) ማጽናኛን በተመለከተ ላሜሕ ምን ትንቢት ተናገረ?
6 ይሖዋ የሰው ልጅን ለዓመፅ ባነሣሣው ፍጡር ላይ ፍርድ በሰጠበት ጊዜ ‘ማጽናኛ የሚሰጥ አምላክ’ መሆኑን አረጋግጧል። (ሮሜ 15:5) ይህን ያደረገው የአዳምን ዘሮች የአዳም ዓመፅ ካስከተለባቸው ጠንቅ የሚያላቅቅ “ዘር” እንደሚልክ ቃል በመግባት ነው። (ዘፍጥረት 3:15) ከጊዜ በኋላም አምላክ ነጻ ስለሚያወጣበት መንገድ አንዳንድ ፍንጮች መስጠት ጀመረ። ለምሳሌ ያህል በአዳም ልጅ በሴት በኩል የአዳም የሩቅ ዘመድ የሆነው ላሜሕ ልጁ ስለሚያደርገው ነገር የሚከተለውን ትንቢት በመንፈስ አነሳሽነት እንዲናገር አድርጎታል፦ “እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል።” (ዘፍጥረት 5:29) ከዚህ ከተሰጠው ተስፋ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ልጁ “ዕረፍት” ወይም “መጽናኛ” የሚል ትርጉም ያለው ኖኅ የሚል ስም ተሰጠው።
-
-
መጽናናትን ለማግኘት ይሖዋን ተስፋ አድርግመጠበቂያ ግንብ—1996 | ኅዳር 1
-
-
8 ይሖዋ ያን ክፉ ዓለም ምድር አቀፍ በሆነ የጥፋት ውኃ ለማጥፋት ወሰነ፤ በመጀመሪያ ግን ሕይወትን ለማዳን ሲል ኖኅን መርከብ እንዲሠራ አደረገው። በዚህ መንገድ የሰው ዘርና የተለያዩ የእንስሳት ዝርያዎች ከጥፋቱ ሊተርፉ ቻሉ። ኖኅና ቤተሰቡ ከጥፋቱ ውኃ በኋላ ከመርከቡ ውስጥ ወጥተው ወደ ጸዳችው ምድር ሲገቡ እንዴት ያለ እፎይታ ተሰምቷቸው ይሆን! በምድር ላይ ደርሶ የነበረው እርግማን ተወግዶ የእርሻ ሥራ ይበልጥ ቀላል ሆኖ ማግኘት ምንኛ የሚያጽናና ነው! በእርግጥም የላሜሕ ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቷል፤ ኖኅም ከስሙ ትርጉም ጋር የሚስማማ ሥራ ሠርቷል። (ዘፍጥረት 8:21) ኖኅ የአምላክ ታማኝ አገልጋይ እንደ መሆኑ መጠን ለሰው ዘር መጠነኛ የሆነ “መጽናኛ” በማምጣት ረገድ የጎላ ሚና ተጫውቷል። ይሁን እንጂ ሰይጣንና አጋንንት መላእክቱ የሚያሳድሩት መጥፎ ተጽዕኖ ከጥፋት ውኃው ጋር አብሮ አልተወገደም፤ የሰው ዘርም በኃጢአት፣ በበሽታና በሞት ቀንበር በመቃተት ላይ ይገኛል።
-