-
የአንባብያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥቅምት 15
-
-
የሕይወታችን ባለቤት የሆነው ይሖዋ ደም መበላት እንደሌለበት ደንግጓል። (ዘፍጥረት 9:3, 4) ደም ሕይወትን ስለሚወክል አምላክ ለጥንቱ የእስራኤል ሕዝብ በሰጠው ሕግ በደም አጠቃቀም ላይ ገደብ አውጥቷል። “የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ . . . በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት” ሲል ደንግጓል። አንድ ሰው ለምግብነት ብሎ እንስሳ ቢያርድስ? አምላክ “ደሙን ያፈስሳል በአፈርም ይከድነዋል” ብሏል።a (ዘሌዋውያን 17:11, 13) ይሖዋ ይህን ትእዛዝ በተደጋጋሚ ተናግሯል። (ዘዳግም 12:16, 24፤ 15:23) ሶንሲኖ ሹማሽ የተባለው የአይሁዳውያን መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- “ደሙ መቀመጥ የለበትም። ከዚህ ይልቅ ለመብልነት እንዳይውል ምድር ላይ መፍሰስ አለበት።” ማንኛውም እስራኤላዊ ሕይወቱ የአምላክ ንብረት የሆነውን የሌላ ፍጡር ደም መውሰድ፣ ማስቀመጥ ወይም መጠቀም አይችልም ነበር።
-
-
የአንባብያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥቅምት 15
-
-
አልፎ አልፎ አንድ ዶክተር አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የራሱን የታካሚውን ደም መልሶ መስጠት ይችል ዘንድ ቀዶ ሕክምና ከመከናወኑ ከሳምንታት በፊት ታካሚው የራሱን ደም እንዲሰጥ (ከቀዶ ሕክምና በፊት የራስን ደም መለገስ ወይም ፒ ኤ ዲ) ያሳስበዋል። ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ ደምን የመውሰድ፣ የማስቀመጥና የመስጠት ልማድ ዘሌዋውያንና ዘዳግም ላይ የሠፈረውን ሕግ በቀጥታ ይቃረናል። ደም መቀመጥ የለበትም፤ ከዚህ ይልቅ ምድር ላይ መፍሰስ አለበት። ይህም በምሳሌያዊ አነጋገር ወደ አምላክ የተመለሰ ያህል ነው። በአሁኑ ጊዜ የሙሴ ሕግ የተሻረ መሆኑ እውነት ነው። ሆኖም የይሖዋ ምሥክሮች አምላክ በሙሴ ሕግ ውስጥ ያካተተውን መሠረታዊ ሥርዓት የሚያከብሩ ሲሆን ‘ከደም ለመራቅም’ ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል። ከዚህ የተነሳ ደም አንሰጥም እንዲሁም ‘መፍሰስ’ ያለበትን የራሳችንን ደም መልሰን ለመውሰድ ብለን አናስቀምጥም። ይህ ድርጊት ከአምላክ ሕግ ጋር ይጋጫል።
-
-
የአንባብያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥቅምት 15
-
-
a ፕሮፌሰር ፍራንክ ኤች ጎርማን እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል:- “ደምን መሬት ላይ ማፍሰስ ግለሰቡ ለእንስሳው ሕይወት እንዲሁም ሕይወት ለሰጠውና እንክብካቤ ለሚያደርግለት አምላክ አክብሮት እንዳለው የሚያሳይ ድርጊት እንደሆነ ይቆጠራል።”
-