-
ለአምላክ የልቧን አውጥታ ነገረችውመጠበቂያ ግንብ—2010 | ሐምሌ 1
-
-
ሐና ለጉዞ በሚደረጉት መሰናዶዎች ራሷን በማስጠመድ ችግሯን ለመርሳት እየሞከረች ነው። በመሠረቱ ወቅቱ የደስታ ጊዜ ሊሆን ይገባ ነበር፤ ባሏ ሕልቃና በሴሎ በሚገኘው የማደሪያ ድንኳን አምልኮ ለማቅረብ በየዓመቱ መላ ቤተሰቡን ይዞ የመሄድ ልማድ ነበረው። ይሖዋ እንዲህ ያሉት ወቅቶች ሕዝቡ የሚደሰትባቸው እንዲሆኑ ይፈልግ ነበር። (ዘዳግም 16:15) ሐናም ከልጅነቷ ጀምሮ በእነዚህ በዓላት ትደሰት እንደነበረ ጥርጥር የለውም። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነገሮች እንደ ቀድሞው አልሆኑላትም።
-
-
ለአምላክ የልቧን አውጥታ ነገረችውመጠበቂያ ግንብ—2010 | ሐምሌ 1
-
-
ገና በማለዳው ቤተሰቡ ሽር ጉድ ይላል። ሁሉም ሰው፣ ልጆችም እንኳ ሳይቀሩ ለጉዞው እየተዘጋጁ ነው። በተራራማው የኤፍሬም ምድር የሚኖረው ይህ ትልቅ ቤተሰብ ወደ ሴሎ ለመድረስ አቀበት ቁልቁለት የሚበዛውን የ30 ኪሎ ሜትር መንገድ መጓዝ ነበረበት።c ጉዞው በእግር አንድ ወይም ሁለት ቀን ይፈጃል። ሐና፣ በዚህ ወቅት ጣውንቷ እሷን ለማናደድ ምን እንደምታደርግ ብታውቅም ጉዞውን ትታ ቤት አልቀረችም። በዚህ መንገድ በዛሬው ጊዜ ላሉት የአምላክ አገልጋዮች ግሩም ምሳሌ ትታለች። ሌሎች የሚፈጽሙት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ለአምላክ የምናቀርበውን አምልኮ እንዲነካብን መፍቀድ ፈጽሞ ጥበብ አይደለም። አለበለዚያ መጽናት እንድንችል እኛን ለማጠንከር የተደረጉት ዝግጅቶች ያመልጡናል።
-
-
ለአምላክ የልቧን አውጥታ ነገረችውመጠበቂያ ግንብ—2010 | ሐምሌ 1
-
-
c ይህ ርቀት የተሰላው የሕልቃና የትውልድ ከተማ የሆነችው ራማ በኢየሱስ ዘመን አርማትያስ በመባል ትታወቅ የነበረችው ከተማ ሳትሆን እንደማትቀር ታስቦ ነው።
-