-
ኤልሳዕ የእሳት ሠረገሎችን አይቷል አንተስ ይታዩሃል?መጠበቂያ ግንብ—2013 | ነሐሴ 15
-
-
ኤልሳዕ ያየው ነገር
ኤልሳዕ የኤልያስን መንፈስ በእጥፍ ለማግኘት ላቀረበው ልመና አምላክ ምን ምላሽ ሰጠ? ዘገባው እንደሚከተለው በማለት ይናገራል፦ “እያዘገሙም ሲነጋገሩ ሳለ፣ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ። ኤልሳዕም ይህን [አየ]።”a ኤልሳዕ ላቀረበው ልመና ይሖዋ የሰጠው መልስ ይህ ነበር። ኤልሳዕ፣ ኤልያስ ከእሱ ሲወሰድ ስላየው የኤልያስን መንፈስ በእጥፍ ተቀበለ፤ እንዲሁም የነቢዩ መንፈሳዊ ወራሽ ሆነ።—2 ነገ. 2:11-14
-
-
ኤልሳዕ የእሳት ሠረገሎችን አይቷል አንተስ ይታዩሃል?መጠበቂያ ግንብ—2013 | ነሐሴ 15
-
-
ኤልያስ በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ባረገበት ወቅት ኤልሳዕ የተመለከተውን ነገር ፈጽሞ እንደማይረሳው ጥርጥር የለውም። ደግሞም እኮ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች ማየት የተለመደ ነገር አይደለም! እነዚህ ነገሮች ይሖዋ፣ ለኤልሳዕ የጠየቀውን ነገር እንደሰጠው የሚያሳዩ ናቸው። እርግጥ ነው፣ በዛሬው ጊዜ አምላክ ለጸሎታችን ምላሽ ሲሰጠን የእሳት ሠረገሎችና ፈረሶችን በራእይ አናይም። ያም ቢሆን አምላክ ፈቃዱን ለማስፈጸም ታላቅ ኃይሉን እንደሚጠቀም ማስተዋላችን አይቀርም። ደግሞም ይሖዋ የድርጅቱን ምድራዊ ክፍል እየባረከው መሆኑን እየተመለከትን ነው፤ ይህም የይሖዋ ሰማያዊ ሠረገላ ወደፊት ሲሄድ ‘የምናየው’ ያህል ነው።—ሕዝ. 10:9-13
-
-
ኤልሳዕ የእሳት ሠረገሎችን አይቷል አንተስ ይታዩሃል?መጠበቂያ ግንብ—2013 | ነሐሴ 15
-
-
a ኤልያስ ያረገው መንፈሳዊ አካል የሆኑት ይሖዋና መላእክቱ ወደሚኖሩበት ሰማይ አይደለም። የመስከረም 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 15ን ተመልከት።
-