-
ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለችበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
18. (ሀ) መርዶክዮስ ለሐማ ለመስገድ ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረው ለምን ሊሆን ይችላል? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።) (ለ) በዛሬው ጊዜ አምላክን በታማኝነት የሚያገለግሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የመርዶክዮስን ምሳሌ የሚከተሉት እንዴት ነው?
18 ሐማ የሚባል አንድ ሰው በጠረክሲስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ተሰጠው። እንዲያውም ንጉሡ ዋነኛ አማካሪው በማድረግና በግዛቱ ውስጥ ሁለተኛውን የሥልጣን ቦታ በመስጠት ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾመው። ከዚህም በላይ ንጉሡ፣ ሰዎች ለዚህ ባለሥልጣን እንዲሰግዱለት ትእዛዝ አስተላለፈ። (አስ. 3:1-4) ይህ ሕግ በመርዶክዮስ ላይ ችግር ፈጠረበት። ንጉሡን መታዘዝ እንዳለበት ያምናል፤ ይሁንና ይህን ለማድረግ ሲል የአምላክን ትእዛዝ መጣስ እንደሌለበትም ያውቃል። ሐማ አጋጋዊ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል። ይህም ሲባል ሐማ የአማሌቃውያን ንጉሥ የነበረውና የአምላክ ነቢይ የሆነው ሳሙኤል የገደለው የአጋግ ዝርያ ነው ማለት ነው። (1 ሳሙ. 15:33) አማሌቃውያን እጅግ ክፉ ከመሆናቸው የተነሳ የይሖዋና የእስራኤላውያን ጠላቶች ሆነው ነበር። አማሌቃውያን በብሔር ደረጃ አምላክ ጥፋት የወሰነባቸው ሕዝቦች ነበሩ።c (ዘዳ. 25:19) ታዲያ አንድ ታማኝ አይሁዳዊ ለአንድ አማሌቃዊ እንዴት ሊሰግድ ይችላል? መርዶክዮስ ይህን ሊያደርግ አይችልም። ደግሞም ከአቋሙ ፍንክች አላለም። ዛሬም ቢሆን አምላክን በታማኝነት የሚያገለግሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ቢሆንም እንኳ “ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዥያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል” የሚለውን መመሪያ በጥብቅ ይከተላሉ።—ሥራ 5:29
-