-
የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
ምዕራፍ 08
የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህ
ይሖዋ በደንብ እንድታውቀው ይፈልጋል። ለምን? ምክንያቱም ስለ ባሕርያቱ፣ ስለ ዓላማውና አንዳንድ ነገሮችን ስለሚያከናውንበት መንገድ ይበልጥ ባወቅክ መጠን የእሱ ወዳጅ ለመሆን ያለህ ፍላጎትም ሊጨምር እንደሚችል ያውቃል። በእርግጥ የአምላክ ወዳጅ መሆን ይቻላል? (መዝሙር 25:14ን አንብብ።) የእሱ ወዳጅ ለመሆን ምን ማድረግ ይኖርብሃል? መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፤ በተጨማሪም ከይሖዋ ጋር የምትመሠርተው ወዳጅነት ከየትኛውም ወዳጅነት የላቀ የሆነበትን ምክንያት ይገልጻል።
1. ይሖዋ ምን ግብዣ አቅርቦልሃል?
“ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።” (ያዕቆብ 4:8) ይህ ምን ማለት ነው? ይሖዋ የእሱ ወዳጅ እንድትሆን ግብዣ አቅርቦልሃል። አንዳንዶች ከማያዩት አካል ጋር ወዳጅ መሆን እንደማይቻል ይሰማቸዋል፤ ከአምላክ ጋር ወዳጅ መሆንማ ጨርሶ የማያስቡት ነገር ነው። ይሖዋ ግን ወደ እሱ እንድንቀርብ ስለሚፈልግ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እሱ ማወቅ የሚያስፈልገንን ነገር በሙሉ አስፍሮልናል። ይሖዋን አይተነው የማናውቅ ቢሆንም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሰፈረልንን መልእክት ስናነብ ከእሱ ጋር ያለን ወዳጅነት ይበልጥ ይጠናከራል።
2. ይሖዋ ከማንም የተሻለ ወዳጅ የሆነው ለምንድን ነው?
የይሖዋን ያህል የሚወድህ የለም። ደስተኛ እንድትሆንና እርዳታ በሚያስፈልግህ ጊዜ ሁሉ ወደ እሱ እንድትጸልይ ይፈልጋል። ‘የሚያስጨንቅህን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ መጣል’ ትችላለህ፤ ‘ምክንያቱም እሱ ስለ አንተ ያስባል።’ (1 ጴጥሮስ 5:7) ይሖዋ ምንጊዜም ቢሆን ወዳጆቹን ለመደገፍ፣ ለማጽናናትና ለማዳመጥ ዝግጁ ነው።—መዝሙር 94:18, 19ን አንብብ።
3. የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
ይሖዋ ሁሉንም ሰዎች ይወዳል፤ ‘የጠበቀ ወዳጅነት ያለው ግን ከቅኖች ጋር ነው።’ (ምሳሌ 3:32) ይሖዋ ወዳጆቹ በእሱ ፊት ጥሩ የሆኑትን ነገሮች እንዲያደርጉና በእሱ ፊት መጥፎ ከሆኑ ነገሮች እንዲርቁ ይፈልጋል። አንዳንዶች ይሖዋ ጥሩና መጥፎ የሆነውን ነገር በተመለከተ ያወጣውን መሥፈርት ፈጽሞ ሊያሟሉ እንደማይችሉ ይሰማቸው ይሆናል። ሆኖም ይሖዋ ያለብንን የአቅም ገደብ ይረዳል። ከልባችን እስከወደድነውና እሱን ለማስደሰት የምንችለውን ሁሉ እስካደረግን ድረስ ይቀበለናል።—መዝሙር 147:11፤ የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35
ጠለቅ ያለ ጥናት
የይሖዋ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነና ይሖዋ ከማንም የተሻለ ወዳጅ ይሆንልሃል የምንለው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።
4. አብርሃም የይሖዋ ወዳጅ ነበር
ስለ አብርሃም (አብራም ተብሎም ተጠርቷል) የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ የአምላክ ወዳጅ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ያስችለናል። በዘፍጥረት 12:1-4 ላይ የሚገኘውን ስለ አብርሃም የሚገልጽ ዘገባ አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ አብርሃምን ምን እንዲያደርግ ጠይቆታል?
ይሖዋ ለአብርሃም ምን ቃል ገብቶለታል?
አብርሃም ይህ ትእዛዝ ሲሰጠው ምን አደረገ?
5. ይሖዋ ከወዳጆቹ የሚጠብቃቸው ነገሮች
ማናችንም ብንሆን ከጓደኞቻችን አንዳንድ ነገሮች መጠበቃችን አይቀርም።
አንተ ጓደኞችህ እንዲያደርጉ የምትፈልጋቸው አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?
አንደኛ ዮሐንስ 5:3ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ወዳጆቹ ምን እንዲያደርጉ ይፈልጋል?
ይሖዋን ለመታዘዝ በምግባራችን ወይም በባሕርያችን ላይ ለውጥ ማድረግ ሊያስፈልገን ይችላል። ኢሳይያስ 48:17, 18ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ወዳጆቹ አንዳንድ ለውጦችን እንዲያደርጉ የሚፈልገው ለምንድን ነው?
6. ይሖዋ ለወዳጆቹ የሚያደርጋቸው ነገሮች
ይሖዋ ወዳጆቹ ያጋጠሟቸውን ችግሮች መቋቋም እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ በቪዲዮው ላይ የታየችው ሴት የነበራትን አሉታዊ አስተሳሰብና ስሜት እንድታሸንፍ የረዳት እንዴት ነው?
ኢሳይያስ 41:10, 13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ለወዳጆቹ ሁሉ ምን እንደሚያደርግላቸው ቃል ገብቷል?
ይሖዋ ጥሩ ወዳጅ የሚሆንህ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?
7. የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን ከእሱ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል
ወዳጅነት ሊጠናከር የሚችለው ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ሲኖር ነው። መዝሙር 86:6, 11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋን ማነጋገር የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ እኛን የሚያነጋግረን እንዴት ነው?
አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ከአምላክ ጋር ወዳጅነት መመሥረት የማይቻል ነገር ነው።”
የይሖዋ ወዳጅ መሆን እንደምንችል ለማስረዳት የትኛውን ጥቅስ ትጠቀማለህ?
ማጠቃለያ
ይሖዋ ወዳጅህ መሆን ይፈልጋል፤ ደግሞም ወደ እሱ እንድትቀርብ ይረዳሃል።
ክለሳ
ይሖዋ ወዳጆቹን የሚረዳቸው እንዴት ነው?
ይሖዋ ወዳጆቹ አንዳንድ ለውጦችን እንዲያደርጉ የሚፈልገው ለምንድን ነው?
የይሖዋ ወዳጅ መሆን ከአቅም በላይ የሆነ ነገር እንደሆነ ይሰማሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?
ምርምር አድርግ
ከይሖዋ ጋር ወዳጅነት መመሥረትህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?
የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ አንብብ።
“የአምላክ ወዳጅ መሆን የምችለው እንዴት ነው?” (ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2፣ ምዕራፍ 35)
አንዲት ሴት ከይሖዋ ጋር ወዳጅነት መመሥረቷ የጠቀማት እንዴት እንደሆነ አንብብ።
ወጣቶች ከይሖዋ ጋር ስላላቸው ወዳጅነት ምን እንደሚሰማቸው ሲናገሩ አዳምጥ።
-
-
ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
6. ስንጠመቅ የይሖዋ ቤተሰብ አባል እንሆናለን
ስንጠመቅ አንድነት ያለው ዓለም አቀፍ ቤተሰብ አባል እንሆናለን። ያደግንበት ቦታ ወይም የኋላ ታሪካችን የተለያየ ቢሆንም የምናምንባቸው ነገሮችም ሆኑ የምንመራባቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ተመሳሳይ ናቸው። መዝሙር 25:14ን እና 1 ጴጥሮስ 2:17ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ጥምቀት አንድ ሰው ከይሖዋ ጋርም ሆነ ከሌሎች የይሖዋ አገልጋዮች ጋር ባለው ዝምድና ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?
-
-
አምላክ ለእኛ ያለው ዓላማ ምንድን ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. በዛሬው ጊዜ አስደሳች ሕይወት መምራት የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ የፈጠረን ‘መንፈሳዊ ፍላጎት’ ማለትም እሱን የማወቅና የማምለክ ፍላጎት እንዲኖረን አድርጎ ነው። (ማቴዎስ 5:3-6ን እና የግርጌ ማስታወሻውን አንብብ።) ከእሱ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንድንመሠርት፣ ‘በመንገዶቹ ሁሉ እንድንሄድ፣ እንድንወደው’ እንዲሁም ‘በሙሉ ልባችን እንድናገለግለው’ ይፈልጋል። (ዘዳግም 10:12፤ መዝሙር 25:14) እንዲህ የምናደርግ ከሆነ ችግሮች ቢያጋጥሙንም እውነተኛ ደስታ ማግኘት እንችላለን። ይሖዋን ማምለክ ሕይወታችን ትርጉም ያለውና አስደሳች እንዲሆንልን ያደርጋል።
-