-
ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
5. እንዳትጠመቅ መሰናክል ሊሆኑብህ የሚችሉ ነገሮችን አሸንፍ
ሕይወታችንን ለይሖዋ ለመስጠትና ለመጠመቅ ስንወስን ሁላችንም መሰናክሎች ያጋጥሙናል። አንድ ምሳሌ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
በቪዲዮው ላይ ናራንጌረል ይሖዋን ለማገልገል የትኞቹን መሰናክሎች ማለፍ አስፈልጓታል?
ለይሖዋ ያላት ፍቅር መሰናክሎቹን እንድትወጣ የረዳት እንዴት ነው?
ምሳሌ 29:25ን እና 2 ጢሞቴዎስ 1:7ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
መሰናክሎችን ለመወጣት የሚያስፈልገንን ድፍረት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?
-
-
ስደትን በጽናት መቋቋም ትችላለህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
ከወዲሁ በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት ማጠናከር ያስፈልገናል። በየዕለቱ ወደ ይሖዋ የምትጸልይበትና ቃሉን የምታነብበት ጊዜ መድብ። በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ አዘውትረህ ተገኝ። እነዚህን ነገሮች ማድረግህ የቤተሰብ ተቃውሞን ጨምሮ የሚያጋጥምህን ማንኛውንም ዓይነት ስደት በድፍረት ለመቋቋም ብርታት ይሰጥሃል። በተደጋጋሚ ስደት የደረሰበት ሐዋርያው ጳውሎስ “ይሖዋ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም” በማለት ጽፏል።—ዕብራውያን 13:6
አዘውትረን መስበካችንም ድፍረት ለማዳበር ይረዳናል። የስብከቱ ሥራ በይሖዋ እንድንታመንና የሰው ፍርሃትን እንድናሸንፍ ያሠለጥነናል። (ምሳሌ 29:25) ለመስበክ የሚያስፈልግህን ድፍረት ከወዲሁ ካዳበርክ መንግሥት በሥራችን ላይ እገዳ በሚጥልበት ጊዜም መስበክህን ለመቀጠል ዝግጁ ትሆናለህ።—1 ተሰሎንቄ 2:2
-