ክርስቲያናዊ ሕይወት
‘ባሏ በሰዎች ዘንድ በሰፊው የታወቀ ነው’
ባለሙያ ሚስት ባሏን ታስከብራለች። በንጉሥ ልሙኤል ዘመን፣ ባለሙያ ሚስት ያለው ባል ‘በከተማዋ በሮች በሰዎች ዘንድ በሰፊው ይታወቅ’ ነበር። (ምሳሌ 31:23) በዛሬው ጊዜ፣ የተከበሩ ወንዶች የጉባኤ ሽማግሌዎችና አገልጋዮች ሆነው ያገለግላሉ። ያገቡ ከሆኑ፣ የሚስቶቻቸው መልካም ምግባርና የሚያደርጉላቸው ድጋፍ ጉባኤውን በሚያገለግሉበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። (1ጢሞ 3:4, 11) እንዲህ ያሉት ባለሙያ ሚስቶች የባሎቻቸውን ብቻ ሳይሆን የጉባኤውንም አድናቆት ያተርፋሉ።
አንዲት ባለሙያ ሚስት፣ ባሏ ኃላፊነቱን እንዲወጣ መርዳት የምትችልባቸው መንገዶች፦
ደግነት የሚንጸባረቅባቸው ቃላት ተጠቅማ በማበረታታት።—ምሳሌ 31:26
ባሏ ጉባኤውን ለመርዳት የሚያስችል ጊዜ እንዲኖረው በፈቃደኝነት በመተባበር።—1ተሰ 2:7, 8
ባላት ነገር ረክታ በመኖር።—1ጢሞ 6:8
ጉባኤውን የሚመለከቱ ሚስጥራዊ ጉዳዮችን እንዲነግራት ባለመጠየቅ።—1ጢሞ 2:11, 12፤ 1ጴጥ 4:15