-
‘ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ!’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
3. ይሖዋ “አገልጋዬ” ስላለው ሰው በኢሳይያስ አማካኝነት ምን ትንቢት ተናግሯል?
3 ይሖዋ እርሱ ራሱ የሚመርጠው አንድ አገልጋይ እንደሚመጣ በኢሳይያስ አማካኝነት ትንቢት ተናግሯል። “ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፣ በእርሱም ደስ የሚለኝ [“ነፍሴ የተቀበለችው፣” NW ] ምርጤ ይህ ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል። አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤ ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም። የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤ ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል። ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣ አይደክምም፤ ተስፋም አይቆርጥም፤ ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”—ኢሳይያስ 42:1-4 አ.መ.ት
-
-
‘ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ!’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
7. ትንቢቱ ኢየሱስ ‘እንደማይጮኽ ወይም ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል እንደማያሰማ’ የተናገረው ለምንድን ነው?
7 ይሁንና ትንቢቱ ስለ ኢየሱስ ሲናገር “አይጮኽም፣ ቃሉንም ከፍ አያደርግም፤ ድምፁንም በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም” የሚለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም በዘመኑ እንደነበሩት ብዙ ሰዎች ልታይ ልታይ የሚል ስላልነበረ ነው። (ማቴዎስ 6:5) የሥጋ ደዌ የነበረበትን አንድ ሰው በፈወሰ ጊዜ “ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ” ብሎታል። (ማርቆስ 1:40-44) ኢየሱስ የሰዎችን ትኩረት ከመሳብና ሰዎች በስሚ ስሚ ከደረሳቸው ወሬ ተነሥተው አንድ መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ከማድረግ ይልቅ እርሱ ክርስቶስ ማለትም የተቀባ የይሖዋ አገልጋይ መሆኑን ራሳቸው በተጨባጭ ማስረጃ እንዲያስተውሉ ይፈልግ ነበር።
-