-
“በአለቆች አትታመኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
9. ሴሎ ማን ነው? ምን ዓይነት አስተማሪስ ነው?
9 ብዙ መቶ ዘመናት ካለፉ በኋላ “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ” መሲሑ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ተወለደ። (ገላትያ 4:4፤ ዕብራውያን 1:1, 2) ይሖዋ የቅርብ ረዳቱን ለአይሁዳውያን ቃል አቀባይ አድርጎ መሾሙ ለሕዝቡ ምን ያህል ፍቅር እንዳለው የሚያሳይ ነው። ኢየሱስ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ቃል አቀባይ ሆኖ አገልግሏል! ኢየሱስ ቃል አቀባይ ብቻ ሳይሆን ታላቅ አስተማሪም ነው። በማስተማር ችሎታው አቻ ከማይገኝለት ከይሖዋ አምላክ በቀጥታ የተማረ በመሆኑ ታላቅ አስተማሪ መባሉ ምንም አያስደንቅም። (ዮሐንስ 5:30፤ 6:45፤ 7:15, 16, 46፤ 8:26) ኢየሱስ በኢሳይያስ በኩል የተናገረው ትንቢታዊ ቃል ይህን የሚያረጋግጥ ነው:- “የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፣ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።”—ኢሳይያስ 50:4b
10. ኢየሱስ ይሖዋ ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር የሚያንጸባርቀው እንዴት ነው? ሕዝቡስ ምን ዓይነት ምላሽ ይሰጣሉ?
10 ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት በሰማይ ከአባቱ ጋር ይሠራ ነበር። በአባቱና በልጁ መካከል ያለው የጠበቀ ወዳጅነት በምሳሌ 8:30 ላይ በግጥም መልክ ተገልጿል:- “እኔ [በይሖዋ] ዘንድ ዋና ሠራተኛ ነበርሁ፤ . . . በፊቱም ሁልጊዜ ደስ ይለኝ ነበርሁ።” ኢየሱስ አባቱን መስማቱ ከፍተኛ ደስታ አስገኝቶለታል። አባቱ ያሳየውን ፍቅር እርሱም ‘ለሰው ልጆች’ አሳይቷል። (ምሳሌ 8:31) ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመጣ ‘የደከመውን በቃል ይደግፋል።’ አገልግሎቱን የሚጀምረው በኢሳይያስ ትንቢት ላይ የሚገኘውን የሚከተለውን አጽናኝ ቃል በማንበብ ነው:- “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ . . . የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ።” (ሉቃስ 4:18፤ ኢሳይያስ 61:1) ለድሆች የምሥራች ያበስራል! ለደከሙት እረፍትን ይሰጣል! ይህ መግለጫ ሕዝቡን እጅግ ሊያስደስታቸው የሚገባ ቢሆንም መግለጫውን ሲሰሙ የሚደሰቱት ሁሉም አይደሉም። ውሎ አድሮ ብዙዎች ኢየሱስ በይሖዋ የተማረ መሆኑን የሚያሳዩትን ማስረጃዎች አምነው ለመቀበል አሻፈረን ይላሉ።
11. ከኢየሱስ ጋር ቀንበሩን የሚሸከሙት እነማን ናቸው? ይህስ ምን ያስገኝላቸዋል?
11 ይሁን እንጂ አንዳንዶች ይበልጥ ለመማር ልባቸው ይነሳሳል። ኢየሱስ የሚያቀርበውን የሚከተለውን ከልብ የመነጨ ጥሪ በደስታ ይቀበላሉ:- “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።” (ማቴዎስ 11:28, 29) ወደ ኢየሱስ ከሚመጡት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ሐዋርያቱ ይሆናሉ። ከኢየሱስ ጋር ቀንበሩን መሸከማቸው ከባድ ሥራ እንደሚያስከትልባቸው ያውቃሉ። ይህ ሥራ የመንግሥቱን ምሥራች እስከ ምድር ዳር ድረስ መስበክን ይጨምራል። (ማቴዎስ 24:14) ሐዋርያቱም ሆኑ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት በዚህ ሥራ መሳተፍ ሲጀምሩ በእርግጥም ለነፍሳቸው እረፍት የሚያመጣ መሆኑን ይገነዘባሉ። በዘመናችን ያሉ ታማኝ ክርስቲያኖችም ይህን ሥራ በማከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ሥራ መካፈላቸው ተመሳሳይ የሆነ ደስታ አስገኝቶላቸዋል።
-
-
“በአለቆች አትታመኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
b ጸሐፊው ከኢሳ. 50 ቁጥር 4-11 ጀምሮ እስከ ምዕራፉ መጨረሻ ድረስ ባሉት ቁጥሮች ላይ ስለራሱ እየተናገረ ያለ ይመስላል። ኢሳይያስ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ ከተጠቀሱት ፈተናዎች መካከል አንዳንዶቹ በራሱ ላይ ደርሰውበት ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ትንቢቱ ሙሉ በሙሉ ፍጻሜውን ያገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ነው።
-